በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩጋንዳው ሁለት ፍንዳታዎች ሦስት ሰዎች ሞቱ 33 ቆሰሉ


ዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ውስጥ አንድ የፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያና የሃገሪቱ ምክር ቤት ህንጻ በሚገኝበት ጎዳና ላይ ፍንዳታዎች ደረሱ
ዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ውስጥ አንድ የፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያና የሃገሪቱ ምክር ቤት ህንጻ በሚገኝበት ጎዳና ላይ ፍንዳታዎች ደረሱ

ዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ውስጥ አንድ የፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያና የሃገሪቱ ምክር ቤት ህንጻ በሚገኝበት ጎዳና ላይ ዛሬ በደረሱ ፍንዳታዎች ቢያንስ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ 33 መቁሰላቸው ተሰማ፡፡

የተቀናጁ በመሰሉ ሁለቱ ፍንዳታዎች የቆሰሉ 33 የሚደርሱ ሰዎች ለህክምና ወደ ሆስፒታል መሄዳቸውን የሃገሪቱ የጤና ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

ከቁስለኞቹ ውስጥ ቢያንስ ሰባቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ፖሊስ ስለ አደጋው ዝርዝር መግለጫ ያልሰጠ ሲሆን ፍንዳታው የቦምብ መሆን አለመሆኑ አለመረጋገጡን አሶሼይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

የዩናጋንዳ ባለሥልጣናት ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ተከታተለው በሚደርሱ የቦምብ ፍንዳታዎች የተነሳ ህዝቡ ጥናቃቄ እንዲያደርግና አካባቢውን እንዲጠባበቅ መክረዋል፡፡

በማዕከላዊ አፍሪካ የሚገኘውና የእስላማዊ መንግሥት ተባባሪ የሆነውና በሃገር ውስጥ የሚንቀሳቀሰው የተባበሩት የዲሞክራሲ ኃይሎች የተባለው ቡድን ባላፈው ወር በአንድ የዩናጋንዳ ምግብ ቤት ውስጥ ለደረሰው ፍንዳታ ኃላፊነቱን መውሰዱ ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG