በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትራምፕና ባይደን የመጨረሻውን ዙር ተከራከሩ


ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዴሞክራቲኩ ተፎካካሪያቸው የቀድሞ ም/ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በመጨረሻው ፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ክርክር ወቅት
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዴሞክራቲኩ ተፎካካሪያቸው የቀድሞ ም/ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በመጨረሻው ፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ክርክር ወቅት

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና የዴሞክራቲክ ፓርቲው ተፎካካሪያቸው ጆ ባይደን በናሽቪል ቴነሲ፣ ትናንት ሀሙስ ምሽት፣ ለመጨረሻው ዙር፣ ፕሬዚዳንታዊ ክርክር ተገናኝተዋል፡፡ ክርክሩን የተከታተለው የቪኦኤ ዘጋቢ ማይክ ኦስሊቪያን ዘገባ ይዘናል።

የመጨረሻውና ሁለተኛ ዙር ክርክር የተሄካደው ለምርጫው ከሁለት ሳምንት ያነሰ ጊዜ ሲቀረው ነው፡፡ የመጀመሪያው አከራካሪ ጥያቄ የኮቪድ - 19 ጉዳይ ነበር፡፡ክርክሩ ትራምፕ በሰጡት መልስ ነበር የጀመረው፡፡

ትራምፕ “ክትባቱ በቅርብ ዝግጁ ይሆናል” ብለዋል፡፡ ባይደን ግን ታዲያ ምን ያደርጋል “ከ220ሺ በላይ አሜሪካውያን ከሞቱ በኋላ” ዘግይቷል ይላሉ፡፡

ሁለቱም ሰዎች፣ አንዳቸው አንዳቸውን በሙስና ወንጅለዋል፡፡ ትራምፕየባይደን ልጅ በሆኑት ሃንተር ባይደን፣ በዩክሬን እና ሩሲያ ተፈጽሟል ስለተባለው የንግድ ሥራ በማንስት የሚክተለውን ተናግረዋል፡፡

“ሁሉም ኢሜሎች፣ ኢሜሎቹ፣ አስከፊዎቹ ኢሜሎች፣ እርስዎና ቤተሰብዎችዎ ስለ ዛቁት ገንዘብ ... እንዴ ጆ!... ከነዚህ አንዳንዶቹ ነገር ሲፈጸሙ እኮ እርስዎ ምክትል ፕሬዚዳንት ነበሩ”

ባይደን ውንጀላውን እንዲህ በማለት አስተባብለዋል፡፡

“በህይወቴ ከውጭ ካለ ምንጭ፣ አንዲት ሳንቲም አልወሰድኩም፡፡ በፍጹም! እኚህ ፕሬዚዳንት ግን ለቻይና፣ 50 ጊዜ ግብር መክፈላቸውን፣ በቻይና ባንክ የሚስጥር አካውንት የከፈቱ መሆናቸውን፣ በቻይና ንግድ ያላቸው መሆኑን አውቀናል፡፡”

ትራምፕ በበኩላቸው፣ በመላው ዓለም ንግድ የሚያካሂዱ ሰው በመሆናቸው፣ የቻይናው ባንክ አካውንት “ምስጢር አይደለም” ብለዋል፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ፣ በቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ ግብር ከፍለው የማያውቁ መሆኑን፣ ወይም የከፈሉት እጅግ አነስተኛ መሆኑን አስመልከቶ፣ በቅርቡ ይፋ የተደረገውንም ዘገባ እንደሚከተለው አስተባብለዋል፡፡

“ላለፉት የተወሰኑ ዓመታት ግብሬን አስቀድሜ ስከፈል ነበር፡፡ አስር ሚሊዮን ዶላሮች፡፡ አስቀድሜ ነው የከፍልኳቸዋል፡፡”

ክርክሩ የተካሄደው፣ የዩናይትድ ስቴትስ የደህንነት ባለሥልጣናት፣ የውጭ ኃይሎች፣ በአሜሪካ ምርጫ ሂደት ላይ፣ ጣልቃ ለመግባት እየሞከሩ መሆናቸውን ባስጠነቀቁበት ጊዜ ነው፡፡ የዴሞክራቲክ ፓርቲ እጩ፣ ጆ ባይደን፣

“ ሩሲያ ጣልቃ ስትገባ ነበር፡፡ ቻያናም በተወሰነ ደረጃ ነበረችበት፣ አሁን ደግሞ ይኸው ኢራንም የገባችበት መሆኑን አውቀናል፡፡” ብለዋል፡፡

ትራምፕም በበኩላቸው ለውጭ ተቃናቃኞች ጋሬጣ መሆናቸውን ገልጸው ይህን ብለዋል

“ምክንያቱም ሩሲያ ላይ ጠንካራ የሆነ ማንም አልነበረም፡፡ ማዕቀቦቹን በሚመለከት ከኔ በላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ የወሰደ አልነበረም፡፡ በእነዚያ ሁሉ ላይ ደግሞ ኔቶን አስመልከቶ ያደረግኩ ነገር አለ፡፡ የኔቶ አባል አገራት ተጨማሪ 130 ቢሊዮን ዶላር እንዲያስገቡ በማድረግ በዓመት 420 ቢሊዮን ዶላር ይሆናል፡፡ ያ ከራሽያ ለመከላከል እንዲረዳ ነው፡፡”

ከጆርጅ ሜሰን ዩኒቨርስቲ፣ የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት ጀርሚ ሜየር፣ ሁለቱም እጩዎች በክርክሩ ወቅት፣ ጥሩ ሥራ መስራታቸውን ተናግረው፣ ወደ መጨረሻዎቹ 90 ደቂቃዎች ላይ ባይደን አንጸባርቀው መውጣታቸውን ገልጸው እንዲህ ብለዋል

“ወደ መጨረሻው ላይ የተጠየቁትቱ ጥያቄ አለ፡፡ “ይህን ምርጫ ቢያሸንፉ ለርስዎ ድምጽ ላልሰጡ ሰዎች የሚያስተላልፉት መልዕክት ምንድነው?” ተብለው ነበር፡፡ አሁን በፖለቲካችን እያየነው ካለው ጫፍና ጫፍ ከያዘውና ከተመራረዘው በተቃራኒ፣ ሁሉንም ወገን ወደ አንድነት የሚያመጣ መልዕክት ነበር፡፡”

ትራምፕ ጣልቃ ገብተው ለማቋረጥ ያልሞከሩ መሆኑንም ጀርሚ ከገለጹ በኋላ ትራምፕ

“ምን ማድረግ እንደሚፈልጉ ያውቁ ነበር፡፡ ባይደንን በሙስና እየተነቀፈ ካለው ልጃቸው ጋር ተያይዞ የሚነቀፉበትን ነገር ማንሳት ፈልገው ነበር፡፡ እንደሚመስለኝ በዚያ ነገር ራሳቸው ተመልሰው ሳይጎዱ አልቀሩም፡፡” ብለዋል፡፡

አሸናፊው ጠርቶ ያልታወቀበት ይህ ክርክር፣ የብዙ መራጮችን ውሳኔ ይቀይራል ተብሎ እንደማይጠበቅ ጀርሚ ተናግረዋል፡፡ በህዝብ አስተያየት መሰብሰቢያዎቹ መሠረት ባይደን እየመሩ ሲሆን፣ ፉክክሩ፣ የምርጫውን ውጤት ሊወስኑ በሚችሉት፣ በጣት በሚቆጠሩ አሻሚ ክፍለግዛቶች ላይ ያተኮረ፣ መሆኑም ይነገራል፡፡ ወደ 40 ሚሊዮን የሚቆጠሩ አሜሪካውያንም ከወዲሁ ድምጽ መሰጠታቸውም ይታወቃል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ትራምፕና ባይደን የመጨረሻውን ዙር ተከራከሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:41 0:00


XS
SM
MD
LG