በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በወባ በሽታ የተያዙ ሰዎች ተገኙ


ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በወባ በሽታ የተያዙ ሰዎች ተገኙ
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በወባ በሽታ የተያዙ ሰዎች ተገኙ

በዩናይትድ ስቴትስ ፍሎሪዳ እና ቴክሳስ ክፍለ ግዛት ውስጥ አምስት ሰዎች የወባ በሽታ እንደተገኘባቸው መረጋገጡ ታውቋል።

ትንኝ ወለድ የሆነው ይህ ገዳይ በሽታ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ሲገኝ ከ20 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የበሽታዎች ቁጥጥርና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) ከትናንት በስቲያ ሰኞ አስታውቋል፡፡

ፍሎሪዳ ውስጥ በተገኙት አራት ታካሚዎች እና በቴክሳስ በተገኘው አንድ ታማሚ ላይ ላለፉት ሁለት ወራት ምርመራ ሲካሄድ መቆየቱን ሲዲሲ አመልክቷል፡፡

የፍሎሪዳ ግዛት እንዳስታወቀው ለመጀመሪያው ታካሚ ምርመራ የተካሄደው እ.ኤ.አ ግንቦት 26 በሳራሶታ ወረዳ ውስጥ ነው፡፡

የቴክሳስ ባለስልጣናትም እ.ኤ.አ ሰኔ 23 እንዳስታወቁት በካሜሮን ወረዳ አንድ ግለሰብ በበሽታው መያዙን ተናግረዋል ።

የወባ በሽታ እንደ ድንገተኛ ህክምና ተደርጎ እንደሚወሰድ ሰኞ ይፋ ባደረገው ማስጠንቀቂያ የገለጸው ሲዲሲ፣ “ምልክቱ ያለበት ማንኛውም ሰው በአስቸኳይ መመርመር አለበት" ብሏል።

ይሁን እንጂ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለወባ በሽታ የመጋለጡ ዕድል እጅግ አነስተኛ ነው ሲል ሲዲሲ ጨምሮ ገልጿል፡፡ 95 በመቶ የሚሆነው የወባ በሽታ የሚገኘው አፍሪካ ውስጥ መሆኑን ተቋሙ ገልጾ፣ በበሽታው በአብዛኛው የሚያዙት ከአገር ውጭ የሚጓዙ ሰዎች መሆናቸውን አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG