በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቱርክ የእስላማዊ መንግሥት ቡድን መሪን መያዟን አስታወቀች


የቱርክ ፕሬዚዳንት ጣይብ ኤርዶጋን
የቱርክ ፕሬዚዳንት ጣይብ ኤርዶጋን

ቱርክ በቀጠናው የእስላማዊ መንግሥት ቡድን መሪ የሆነውን አቡ አል ሀሰን፣ አል ሃሺሚ አልቋራሺን፣ በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታወቀች፡፡

ዜናውን ትናንት ሀሙስ ያሰራጨው የቱርክ ኦዳቲቪ፣ አልቃራሺ የተያዘው ቱርክ መዲና ኢስታንቡል ውስጥ በሚገኘው አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ፣ የቱርክ ፖሊሶች ያለምንም ተኩስ ልውውጥ ባደረጉት ድንገተኛ ወረራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የእስላማዊ ቡድኑ መሪ ምርመራ እየተደረገለት ሲሆን፣ የቱርክ ፕሬዚዳንት ጣይብ ኤርዶጋን በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ በቁጥጥር ስር የመዋሉን ዜና ይፋ እንደሚያደርጉ ዘገባው አመልክቷል፡፡ ስማቸውን ያልገለጹ ሁለት የቱርክ ባለሥልጣናት ለብሉምበርግ የዜና ማሰራጫ፣ የአልቋራሺ መያዝ አረጋግጠዋል፡፡

የዩናይትድ ባለስልጣናት ግን ስለጉዳዩ ጥንቃቄን መርጠዋል፡፡ የፔንታገን ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ ትናንት ሀሙስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ጉዳዩን ቀኑ ሙሉ ሲከታተሉት የዋሉት መሆኑን ጠቅሰው፣ ይሁን እንጂ “ስለ አልቋራሺ የተባለውን ሪፖርት ማረጋገጥ አልቻልንም” ብለዋል፡፡

የእስላማዊ መንግሥት ቡድኑ ባለፈው መጋቢት አልቋራሺን መሪው አድርጎ የሾመው፣ የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ኃይል ባላፈው የካቲት፣ በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ባደረገው ጥቃት፣ የቡድኑን የቀድሞ መሪ ከገደለ በኋላ መሆኑ ተመልከቷል፡፡

XS
SM
MD
LG