በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቱኒዝያዊያን በአዲስ ህገ መንግሥት ላይ ድምፅ ሰጡ

ቱኒዝያዊያን ለፕሬዚዳንት ካዪስ ሳዒድ ተጨማሪ ሥልጣን ይሰጣል በተባለ አዲስ ህገ መንግሥት ላይ የውሳኔ ህዝብ ድምፃቸውን ዛሬ ሲሰጡ ውለዋል።
ቱኒዝያዊያን ለፕሬዚዳንት ካዪስ ሳዒድ ተጨማሪ ሥልጣን ይሰጣል በተባለ አዲስ ህገ መንግሥት ላይ የውሳኔ ህዝብ ድምፃቸውን ዛሬ ሲሰጡ ውለዋል።

ቱኒዝያዊያን ለፕሬዚዳንት ካዪስ ሳዒድ ተጨማሪ ሥልጣን ይሰጣል በተባለ አዲስ ህገ መንግሥት ላይ የውሳኔ ህዝብ ድምፃቸውን ዛሬ ሲሰጡ ውለዋል።

ፕሬዚዳንቱ ሀገሪቱን ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች ለመታደግ እርምጃ መውሰድ አለብኝ በማለት ከአንድ ዓመት በፊት ፓርላማውን ማገዳቸው ይታወሳል።

ነቃፊዎች አዲሱን ሀገ መንግሥት ‘ፕሬዚዳንቱ ሥልጣን ጠቅልለው ራሳቸው ሊይዙ ያደረጉት ነው’ በማለት የወቀሱ ሲሆን ከዛሬው ውሳኔህዝብ በፊት በነበሩት ቀናትም የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ተካሂደዋል።

ተቃዋሚ ፓርቲዎችና የሲቪል ማኅበረሰብ ቡድኖች ህዝቡ እንዳይሳተፍ ቅስቀሳ ቢያካሂዱም አዲሱ ህገ መንግሥት “በቂ የድጋፍ ድምፅ አግኝቶ ያልፋል’ ተብሎ እንደሚጠበቅ ዜናው ጨምሮ አመልክቷል።

ለውሳኔ ህዝብ የቀረበው አዲሱ ህገ መንግሥት ለፕሬዚዳንት ሳዒድ ሁሉንም የሥራ አስፈጻሚ ሥልጣንና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥነቱን የሚሰጣቸው ሲሆን የፓርላማ ይሁንታ ሳያስፈልጋቸው ሹመቶች እንዲሰጡም ይፈቅድላቸዋል።

XS
SM
MD
LG