በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቱኒዝያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ፕሬዚዳንቱን በመቃወም አደባባይ ወጡ


በቱኒዚያ ዋና ከተማ በትናንትናው እለት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ፕሬዚዳንት ኪያስ ሰኢድን በመቃወም ከሥልጣን እንዲወርዱ በመጠየቅ አደባባይ ወጥተዋል
በቱኒዚያ ዋና ከተማ በትናንትናው እለት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ፕሬዚዳንት ኪያስ ሰኢድን በመቃወም ከሥልጣን እንዲወርዱ በመጠየቅ አደባባይ ወጥተዋል

በቱኒዚያ ዋና ከተማ በትናንትናው እለት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ሥልጣን እያከማቹ ነው ያሏቸውን ፕሬዚዳንት ኪያስ ሰኢድን በመቃወም ከሥልጣን እንዲወርዱ በመጠየቅ አደባባይ ወጥተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ፣ በዚህ መጠን የተቀሰቀሰ ህዝባዊ ቁጣ ሲገጥማቸውም የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡

ፕሬዚዳንቱ እኤአ በ2014 የወጣውን አብዛኛውን ህገመንግሥት ወደ ጎን በመተው፣ ጠቅላይ ሚኒስትራቸውን ካባረሩና ምክር ቤቱን ከበተኑ ሁለት ወር በኋላ ለራሳቸው ሙሉ ሥልጣን የሚሰጣቸውን ህግ አውጥተዋል፡፡

ሰልፈኞችም “መፈንቀለ መንግሥቱ እንዲቀር እንፈልጋለን” በማለት አደባባይ ወጥተዋል፡፡

በቱኒዚያ እየታየው ያለው ነገር እኤአ በ2011 ለተቀጣጠለው የአረብ አብዮት መነሻ በሆነው የለውጥ እንቅስቃሴ የተገኙትን ዴሞክራሲያዊ ውጤቶች ያደበዘዘው መሆኑን ተንታኞች ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG