በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቱኒዚያ ፍልሰተኞች አሻጋሪው በቁጥጥር ሥር ዋለ


ከቱኒዚያ የተነሱ ፍልሰተኞች በሜዲትሬንያን ባህር ወደ አውሮፓ ለመሻገር ከእንጨት በተርሰራ ጅልባ ሲጓዙ እና የስፔን መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እርዳታ ሊሰጧቸው ሲደርሱ እአአ ኦገስት 5/2022
ከቱኒዚያ የተነሱ ፍልሰተኞች በሜዲትሬንያን ባህር ወደ አውሮፓ ለመሻገር ከእንጨት በተርሰራ ጅልባ ሲጓዙ እና የስፔን መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እርዳታ ሊሰጧቸው ሲደርሱ እአአ ኦገስት 5/2022

ፍልሰተኞችን በሜዲትሬንያን ባህር ላይ የሚያሻግር ሕገ ወጥ ቡድን አደራጅ ነው በሚል የተጠረጠረን ግለሠብ በቁጥጥር ሥር ማድረጓን ቱኒዚያ ትናንት አስታውቃለች፡፡

ከጣልያን ላምፔዱሳ ደሴት 130 ኪ. ሜ. ርቀት ላይ የምትገኘው ቱኒዚያ፣ ወደ አውሮፓ መሻገር ለሚሹ ፍልሰተኞች ተመራጭ አቋራጭ ነች፡፡

ግለሰቡ 24 በሚሆኑ ክሶች ተከሶ፣ በሌለበት የ79 ዓመት እስራት ተፈርዶበት ነበር።

ከአገሪቱ ወደ አውሮፓ ለሚደረገው ሕገ ወጥ ጉዙ ዋና አስተባባሪ እንደነበር የቱኒዚያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቀዋል።

ባለፈው መስከረም ባህር ላይ ለሰመጡት 20 የሚሆኑ ቱኒዚያውያን ዕልፈትም ተጠያቂ መሆኑን የአገሪቱ የባህር ድንበር ጠባቂ ኃይል አስታውቋል።

የአውሮፓ ኅብረት የድንበር ቁጥጥር ድርጅት እንደሚለው፣ በሜዲትሬንያን በኩል ወደ አውሮፓ የሚደረገው ጉዞ በ300 እጥፍ ማደጉንና፣ 42 ሺሕ 200 ፍልሰተኞች መግባታቸውን ስታውቋል።

XS
SM
MD
LG