በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተቃውሞ ሰልፍ በቱኒዥያ


ፎቶ፦ ፕሬዚዳንቱ ካዪስ ሰኢድ ቱኒዥያ መስከረም 20/2021
ፎቶ፦ ፕሬዚዳንቱ ካዪስ ሰኢድ ቱኒዥያ መስከረም 20/2021

ቱኒዥያ ውስጥ ፕሬዚዳንቱ ካዪስ ሰኢድ የመንግሥት ሥልጣን ጠቅልለው መያዛቸውን እና ከመፈንቅለ መንግሥት የሚቆጠር ያሉትን ተግባር በመቃወም ትናንት ዕሁድ በብዙ መቶዎች የተቆጠሩ ሰዎች ዋና ከተማ ቱኒዥያ ውስጥ ሰልፍ አካሂደዋል።

የትልቁ ፓርቲ የኢናህዳ ደጋፊዎች ህብረት እና ተቃዋሚ መሪዎች ያደራጁት ሰልፍ ሲሆን ፕሬዚዳንቱ ፓርላማውን በትነው የአስተዳደሩን ሥልጣን ጠቅልለው ከያዙ ወዲህ በተከታታይ የተቃውሞ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው።

ሀገሪቱ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ መቆርቆዟ ያስከፋቸው ቱንዥያውያን መጀመሪያ ላይ የፕሬዚዳንቱን እርምጃ የደገፉ ቢሆንም አምባገነን አገዛዝ ሊመለስብን ነው የሚለውን ሥጋትም አባብሶታል።

ከተቃዋሚ ሰልፈኞቹ አንዱ አሊ ቤለዲ፣

"ካዪስ ሰኢድ በራሳቸውም በህዝቡም አከብረዋለሁ ብለው ቃለ መሃላ ባደረጉበት ህገ መንግሥትም ላይ ነው የተነሱት። ይሄ ትክክል ያልሆነ የመንግሥት ግልበጣ ነው፣ በዕውነትም ደግሞ የቱኒዥያን ህዝብ የሚያዋርድ ድርጊት ነው።" ብለዋል።

በትናንቱ ዓመታዊ የሰማዕታት ቀን በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ተቃዋሚዎች እና የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች መካከል ጭቅጭቅ የተፈጠረ ሲሆን የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች ተቃዋሚiዎቹን ከሃዲዎች ብለዋቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ ፓርላማውን ባለፈው እአአ መጋቢት 31 ቀን በይፋ የበተኑት ሲሆን እርምጃቸው የፖለቲካ ቀውሱን አባብሶታል ተቃዋሚዎችም ሀገሪቱ ወደአምባገነን አገዛዝ ልትመለስ ነው በማለት አስጠንቅቀዋል።

XS
SM
MD
LG