በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተቃውሞ በቱኒዚያ


ፎቶ ፋይል፦ የቱኒዚያ ፕሬዚደንት ካይስ ሰኢድ
ፎቶ ፋይል፦ የቱኒዚያ ፕሬዚደንት ካይስ ሰኢድ

ጠቅላይ ሚንስትሩ ተባረሩ፥ ፓርላማው ታገደ

የቱኒዚያ ፕሬዚደንት ጠቅላይ ሚንስትሩን እና ካቢኔአቸውን ትናንት ዕሁድ አባርረዋል።

እርምጃው የፖለቲካ ቀውሱን ያባባሰው ሲሆን በሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች በፕሬዚደንቱ እርምጃ የተደሰቱ ሰዎች ጎዳና ላይ ወጥተው ድጋፋቸውን ገልጸዋል። ተቃዋሚዎች ደግሞ ድርጊቱ ከመፈንቅለ መንግሥት የሚቆጠር ነው በማለት ኮንነውታል።

የቱኒዚያው ፕሬዚደንት ካይስ ሰኢድ አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር እሾም እና እየረዳኝ የስራ አስፈጻሚውን ስልጣን ራሴ እይዘዋለሁ ሲሉ አስታውቀዋል።

አሁን በቱኒዚያ የተፈጠረው ቀውስ ሀገሪቱ እአአ በ2011 በተካሄደው አብዮት ዲሞክራሲያዊ ስርዐት ከመሰረተች ወዲህ ከተከሰቱት ሁሉ ከባድ ፈተና እንደሆነ ተገልጿል።

ዋና ከተማዋ ቱኒዚያ እና ሌሎችም ትላልቅ ከተሞች ውስጥ ነዋሪዎች ጎዳና ላይ ወጥተው በሆታ እና በመኪና ድምጽ ድጋፋቸውን ገልጸዋል።

ፕሬዚደንቱ ውጥረት ላይ ባለው አስተዳደር እና በተከፋፈለው ፓርላማ ላይ የወሰዱት እርምጃ ከህዝቡ በኩል የተሰጠው ድጋፍ ምን ያህል እንደሆን ግልጽ አይደለም። ፕሬዚደንቱም አንድም ሰው የሁከት ተግባር እንዳይፈጽም አስጠንቅቀዋል።

በመንግስቱ ቴሌቭዥን በተላለፈው ንግግራቸው "ማንም መሳሪያ እንዳያነሳ አስጠነቅቃለሁ፥ ጥይት በሚተኩስ ሰው ላይ የጦር ሰራዊታችን በአጸፋው ጥይት ይተኩሳል" ብለዋል።

የፕሬዚደንቱ ንግግር ከተሰማ በኋላ ምክር ቤቱ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ብሄራዊ መዝሙር እየዘመሩ ደስታቸውን በመግለጽ ላይ ሳሉ ወጥተው በርካታ የጦር ሰራዊት መኪናዎች ህንጻውን እንደከበቡት የዐይን ምስክሮች ገልጸዋል።

ባለፈው ዓመት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ያደቀቀው ሲሆን በአሁኑ ወቅትም የቫይረሱ ስርጭት እጅግ እየተባባሰ ሄዷል። ከዚያ አስቀድሞም በሙስና በመንግሥታዊ አገልግሎቶች መዳከም እና ስራ አጥነቱ በመባባሱ ብዙዎች ቱኒዚያውያን በፖለቲካ ስራዐቱ ላይ ዕምነት እንዲያጡ አድርጎ ቆይቷል።

በማህበራዊ መገናኛ የተቀሰቀሰውን የተቃውሞ ጥሪ ከትላልቆቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዳቸውም ያልተቀላቀሉ ቢሆንም ትናንት ዕሁድ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። አብዛኛው ተቃውሞ ያተኮረው በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ በያዘው አክራሪ ያልሆነው እስላማዊ ፓርቲ ኢናህዳ ላይ እንደነበር ታውቋል።

XS
SM
MD
LG