በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከትግራይ ስላልተመለሱት ተሽከርካሪዎች ከለጋሾች ምላሽ እንደሚፈልግ መንግሥት አስታወቀ


ሙፈሪያት ከሚል - የሰላም ሚኒስቴር
ሙፈሪያት ከሚል - የሰላም ሚኒስቴር

ከሰኔ 14 በኋላ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ጭነው ወደ ትግራይ ከገቡት መኪናዎች ውስጥ ከ90 ከመቶ በላይ የሚሆኑት አለመመለሳቸውን የገለጹት የኢትዮጵያ የሠላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል፤ “ከለጋሽ ድርጅቶች ምላሽ እንፈልጋለን” ብለዋል።

“በዚህ ዓይነት የጦርነት ሁኔታ ውስጥ ወደ ክልሉ የገቡ መኪናዎች አልወጡም ማለት ምን ማለት እንደሆነም ግልጽ ነው” ሲሉም ሚኒስትሯ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ትናንት ባሰፈረው የትዊተር መልዕክትም የተጠቀሱት መኪናዎች አለመመለሳቸውን አረጋግጧል። ሁኔታው አሳሳቢ መሆኑንም ገልጿል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ከትግራይ ስላልተመለሱት ተሽከርካሪዎች ከለጋሾች ምላሽ እንደሚፈልግ መንግሥት አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:55 0:00


XS
SM
MD
LG