በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ሰዎች በረሃብ እየሞቱ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ


ፎቶ ፋይል፦ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል
ፎቶ ፋይል፦ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል

በትግራይ ክልል በሚገኙ የጤና ተቋማት ውስጥ "በረሃብ ሳቢያ የሰዎች ሕይወት እያለፈ ነው" ሲሉ የክልሉ ጤና ቢሮ ገለፀ። የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት በአብዛኛው በመፍረሳቸው በረሃብ የተነሳ ታመው ወደ የጤና ተቋማቱ የሚሄዱ ታካሚዎች በቂ አገልግሎት አያገኙም ሲል ቢሮው ጠቅሷል።

በተያያዘም "በመድሃኒት እጥረት ዜጎች ሕይወታቸው እያለፈ ነው" ሲሉ በክልሉ ያሉ የጤና ባለሞያዎች ባለፈው ቅዳሜ በከተማው ሰልፍ ማድረጋቸው ጠቅሶ መቀሌ የሚገኘው ዘጋቢያችን ሙሉጌታ አፅብሃ ባጠናቀረው ዘገባ፤ በሌላ በኩል በመቀሌ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል ልጃቸውን በማስታመም ላይ የሚገኙ አንዲት እናት፤ ልጃቸው በረሃብ ሳቢያ መታመሟን እና እርሳቸውም ችግር ላይ መሆናቸውን ማመልከታቸውን ዘግቧል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በትግራይ ሰዎች በረሃብ እየሞቱ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:04 0:00


XS
SM
MD
LG