በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ ህሙማን በመድሃኒት እጥረት የሞቱ ነው


ፎቶ ፋይል፦ አይደር ሆስፒታል
ፎቶ ፋይል፦ አይደር ሆስፒታል

በኢትዮጵያ ትግራይ ውስጥ ያሉ ዶክተሮች በመንግሥት ለወራት ዝግ በሆነቸው ትግራይ የህክምና መሳሪያዎችና መድሃኒቶች እጥረት በመኖሩ ታማሚዎች ሊድኑ በሚችሉ በሽታዎችን እየሞቱ መሆኑን ትናንት ማክሰኞ ባወጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡

ዶክተሮቹ ባወጡት የጽሁፍ መግለጫ በክልሉ ባለው ትልቁ የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ ያሉ ዶክተሮች የመሳሪያዎች ፣ የደም ስር ፈሳሽ መስጫዎችና ኦክስጂን የመሳሰሉት የህክምና መሳሪያዎች እጠረት መኖሩ የህሙማን ህይወት አስከፍሏል ብለዋል፡፡

በትግራይ ዋና ከተማ መቀሌ የሚገኙ ሀኪሞች በመግለጫቸው የአቅርቦት እጥረት በመኖሩ ባላፉጅት ስድስት ወራት የቀዶ ጥገናና ተያያዥ መሠረታዊ ህክምናዎችን ለመሰጠት “ጨርሶ የማይቻል ሆኗል” ብለዋል፡፡

በዚህ የተነሳም የጭንቅላት ቀዶ ጥገና የሚያስፈልጋቸው ህጻናት እንዲሞቱ ይደረጋል፣ ሊታከም የሚችል ካንሰር ያለባቸው ሰዎች መብታቸው ይነፈጋል ስብራት ያለባቸው ሰዎች ከእንቅስቃሴ ውጭ ሆነው ባሉበት ሆነው እንዲቆዩ ይገደዳሉ፡፡” ብለዋል፡፡

እንደ ሮይተርስ ዘገባ የሆስፒታል ዶክተሮቹ በእጥረቱ የተነሳ 117 ሞትና በተላላፊ በሽታዎች፣ በአካል መቆረጥና በኩላሊት እክል በመሳሰሉት በርካታ የጤና መወሳሰቦች መድረሳቸውን አመልክተዋል፡፡

አንድ ከፍተኛ ዶክተር ከ80 እስከ 90 ከመቶ የሚደርሱ የትግራይ ሆስፒታልን ክሊኒኮች አገልግሎትእየሰጡ አለመሆናቸውን ማስታወቃቸው ተዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ ህወሃት አፍርና አማራ ክልሎችን በኃይል በተቀቶጣጠበረባቸው ወቅት ከክልሉ እንዲወጣ ከመገደዱ በፊት መድሃኒቶችና የህክምና መሳሪያዎችን ከበርካታ ሆስፒታሎችና ከ100 የጤና ማዕከላት የዘረፈ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ህወሃት የተባለውን ያሰተባበል ሲሆን እጥረቱ ከዚያም በፊት የነበረ መሆኑን በመግለጽ መንግስትን ተጠያቂ አድርጓል፡፡

XS
SM
MD
LG