በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታንዛኒያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ


በነገው ዕለት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በምታካሂደው በታንዛኒያ በምርጫው ዙሪያ "የማጭበበር ተግባር እየተፈጸመ ነው" በሚል በተነሳ ተቃውሞ ላይ ፖሊስ ቢያንስ ሰባት ሰዎችን በጥይት ገድሏል ሲል አንድ ዋና የተቃዋሚ ፓርቲ ከሰሰ።

“ዊዛሌንዶ” የተባለው ፓርቲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የከፊል ራስ ገዟ፣ የዛንዚባርን ፕሬዚደንታዊ ዕጩ ማሊም ሃማድንም ፖሊስ አስሯዋል ብሉዋል። የደሴቲቱ ፖሊስም መታሰራቸውን አረጋግጧል። ሰባት ሰው በጥይት ገድላችኋል በተባለው ክስ ጉዳይ ግን ፖሊስ የሰጠው ምላሽ የለም።

ተቃውሚው ፓርቲ በመግለጫው እንዳለው የሃገሪቱ የጦር ሰራዊት አባላት ድምጽ መስጫ ካርዶችን በየምርጫ ጣቢያው በማድረስ ላይ እያለም፣ በአካባቢው የነበሩ ዜጎች

“ካርቶኑ ውስጥ ያሉት ድምጽ የተሰጠባቸው ካርዶች ናቸው” ብለው ምርጫ ጣቢያው እንዳይገቡ ለመከላከል ሲሞክሩ ፖሊስ በአስለቃሽ ጋዝ ለማባረር ሞክሮ፣ በኋላ ግን ጥይት ተኩሶባቸዋል ሲል ተቃዋሚ ፓርቲው ከሷል።

XS
SM
MD
LG