በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታንዛንያ ተቃዋሚዎች የምርጫውን ውጤት አንቀበልም አሉ


ባለፈው ረቡዕ እኤአ ጥቅምት 28፣ መራጮች በታንዛኒያ ዳሬሰላም ለፕሬዝዳንታዊና የተወካዮች ምክር ቤት እጩዎች ድምጻቸውን ሲሰጡ
ባለፈው ረቡዕ እኤአ ጥቅምት 28፣ መራጮች በታንዛኒያ ዳሬሰላም ለፕሬዝዳንታዊና የተወካዮች ምክር ቤት እጩዎች ድምጻቸውን ሲሰጡ

የታንዛንያ ተቃዋሚ ፓርቲ፣ በአገሪቱ የተካሄደውን የምርጫ ከፍተኛ ማጭበርበር የተፈጸመበት በመሆኑ ውጤቱን የማይቀበል መሆኑን አስታውቋል፡፡ ፕሬዚዳንታዊ እጩ ተፎካካሪ የሆኑት ቱንዱ ሊሱ፣ ባለፈው ረቡዕ ከተካሄደው ምርጫ እየተነገረ ያለውን ውጤት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዳይቀበለው ጠይቀዋል፡፡

ባለፈው ረቡዕ የታንዛኒያ መራጮች ድምጻቸውን ከሰጠቡት አንድ ቀን በኋላ ተቀናቃኙ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ቱንዱ ሊሱ፣ ምርጫው የተጭበረበረ መሆኑን በመግለጽ እንደማይቀበሉት ገልጸዋል፡፡ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ውድቅ እንዲያደርገው በመጠየቅ የሚከተለውን ብለዋል

“ዜጎች ይህን ነገር በነቂስ ወጥተው ሰላማዊና ዴሞክራሲዊ በሆነ መንገድ እንዲቃወሙት እየጠየቅን ነው፡፡ ታዛቢዎቻቸውን የላኩ የአገር ውስጥም ሆነ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በተለይም የአፍሪካ ህብረትንም እንዲሁ እየጠየቅን ነው፡፡ ታዛቢዎቻቸውን ወደዚህ የላኩ ሁሉ የምርጫው ውጤት ህጋዊነት የሌለው መሆኑን አውቀው ምንም ዓይነት እውቅና እንዳይሰጡት እንጠይቃለን፡፡”

ገዥው ፓርቲና የመንግሥት ቃለ አቀባዮች የምርጫው ድምጽ ተቆጥሮ እስኪያልቅ ድረስ፣ የሚሰጡት አስተያየት አለመኖሩን ገልዋጸል፡፡ የታንዛኒያ ብሄራዊ ምርጫ ኮሚሽን ሊቀመንበር፣ ሰሚስተክለስ ካዬጄ፣ ስሞታውን ውድቅ አደርገዋል፡፡ “ድምጽ መስጫዎቹ ላይ ጠቋሚ ምልክት ተደርጎባቸዋል” የሚለውን ክስ ዜጎች እንዳይቀበሉት መክረዋል፡፡ “በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚናፈሱ አንዳንድ ወሬዎች ያልተጨበጡና መሠረት የሌላቸው ሲሆን ለምርጫ ኮሚሽኑም እስካሁን የቀረበ ስሞታ አለመኖሩን” ገልጸዋል፡፡

እስካሁን የወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ በፕሬዚዳንት ጃን ሙግፉሊ የሚመራው ገዥዊ ፓርቲ እየመራ ነው፡፡ ፖለቲካ ተንታኙ አቤሴሎም ኪባንዳ፣ “ ከ264 የምርጫ ጣቢያዎች የተሰበሰብው መረጃ እንደሚያሳየው ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥሩ ዜና አይደለም፡፡” ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ​፡፡

የታንዛንያ ተቃዋሚዎች የምርጫውን ውጤት አንቀበልም አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:00 0:00


XS
SM
MD
LG