በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታንዛኒያው ዕጩ የምርጫ ዘመቻቸውን እንዲያቆሙ ታገዱ


ፎቶ ፋይል፦ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተፎካካሪ እጩ፣ ቱንዱ ሊሱ
ፎቶ ፋይል፦ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተፎካካሪ እጩ፣ ቱንዱ ሊሱ

በታንዛኒያ የዴሞክራሲና ተራማጅ ወይም ቻዴማ እየተባለ የሚጠራው ዋነኛው የተቃዋሚ ቡድን አባላት፣ የቡድኑ ዋነኛው የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተፎካካሪ እጩ፣ ቱንዱ ሊሱ፣ የምርጫ ዘመቻቸውን በጊዚያዊነት እንዲቋረጥ መወሰኑን እየተቃወሙ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

ቱንዱ ሊሱ ፣ በመጭው ምርጫ፣ የአገሪቱን ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፍሊንን፣ በዋነኝነት የሚቀናቀኑ እጩ ሆነው የቀረቡ ሲሆን፣ የአገሪቱ ብሄራዊ የምርጫ ኮሚሽን ፣ ሊሱ በርካታ የምርጫ ደንቦችን እየጣሱ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ኮሚሽኑ የምርጫ ዘመቻው እንዲቋረጥ ያቀቡት ጥያቄ ያልተገባ፣ ህገወጥና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የቪኦኤ ዘጋቢ ቻለርስ ኮሜ ከዳሬ ሰላም ዘገባ ልኳል፡፡

የታንዛኒያ የምርጫ ኮሚሽን፣ ከጥቅምት 3 ጀምሮ፣ ለሰባት ቀናት ዋነኛው የምርጫ ተቀናቃኝ ቱንዱ ሊሱ፣ የምርጫ ዘመቻቸውን እንዲያቋርጡ በቅርቡ ያወጣው ውሳኔ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡ ዋነኞቹ የተቃውሚ ቡድን አባላት ከፍተኛ ውግዘት እያሰሙ ሲሆን የምርጫ ኮሚሽኑ ደግሞ ቱንዱ ሊሱ የምርጫ ደንቦችን ተላልፈዋል ይላሉ፡፡ ሳይታቀድ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ህዝብ ይሰብስባሉ በማለትም ወቅሰዋቸዋል፡፡ የተቃውሚ መሪ ሊሱ ግ ን እገዳው የተፈጸመባቸው ተፎካካሪያቸው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ከምርጫ ዘመቻው እረፍት መውሰድ ስለፈለጉ እሳቸው በሌሉበት እኔን ዝም ለማሰኘት ነው ይላሉ፡፡ እንዲህ ይላሉ ሊሱ

“ምን ማደረግ እንደሚፈልጉ ገብቶኛል፡፡ ማግፉሊ በሚያርፍቡት ጊዜ የምርጫ ዘመቻ እንዳላካሂድ ይፈልጋሉ፡፡ ላነሳቸው የምችላቸው ጉዳዮች አስፈርቷቸዋል፡፡ ምክን ያቱም ምንም በቂ ምላሽ የላቸውም፡፡ እና ይሄ እኔን ለማስፈራራት የሚደረግ ነው፡፡ በምንም መንገድ ግን የምቀበለው አይሆንም፡፡”

በቅርቡ በወጣው የምርጫ ኮሚሽኑ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ማጉፊሊ የ8 ቀናት እረፍት አላቸው፡፡ ይህ ደግሞ ሊሱ ከታገዱበት የሰባት ቀናት እገዳ ጋር ይገጣጠማል፡፡ ተቃዋሚዎቹ ይሄ በግልጽ ተቃውሚዎችን ዝም ለማሰኘት የተደረገ ነገር ነው ይላሉ፡፡ ቻዴማ እየተባለ የእሚጠራው ዋነኛው የተቃዋሚ ቡድን አባላት መካከል፣ ኢብራሂም ቻዌ እንዲህ ይላሉ

“ተቃዋሚዎቹና ሊዙ ያላግባብ ለተከሰሱበት ነገር ተጠያቂው ገዥው ፓርቲ ነው፡፡”

ሄለን ሲሳያ የአፍሪካ ወጣቶች ዴሞክራቲክ ህብረት ጋር የሚሰሩ አክቲቪስት ናቸው፡፡ የምርጫ ኮሚሽኑ፣ መንግሥትም የምርጫውን ደንብ ሲተላለፍ ተጠያቂ እንዲሆን ማድረግ አለበት ባይ ናቸው፡፡ እንዲህ ብለዋል

“ ሊሱ ለብሄራዊ ምርጫ አፈጻሚ ኮሚሽን፣ ገዥው ፓርቲ የምርጫውን ደንብ እየጣሰ መሆኑን አስመልከቶ፣ ያለውን ቅሬታ አስታውቃለች፡፡ የምርጫ ኮሚሽኑ ግ ን ነገሩን ችላ ያለው ነው የሚመስለው፡፡”

የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት አዛሊ ሉዌታማ ደግሞ የምርጫ ኮሚሽኑ ገለልተኛ አለመሆኑን እንዲህ በማለት ይናገራሉ፡፡

"የምርጫ ኮሚሽኑ እንደተጠበቀው ገለልተኛ አለመሆኑን በግልጽ አሳውቋል፡፡ ይህን ደግሞ ብዙ ሰዎች ሲናገሩት ነበር፡፡ ስለዚህ፣ አሁን ህዝቡ የምርጫ ኮሚሽኑ ከመንግሥት ጎን መሆኑን አምኖ ስለተቀበለው ፣ ያንን እንደ ህዝብ ድጋፍ በመቁጠር ከዚያ ጀርባ መደበቅን ፈልጓል፡፡”

የምርጫው ኮሚሽን አባላት ደግሞ በበኩላቸው ሊሱ፣ ከምርጫ ዘመቻ እንዲታቀቡ ውሳኔውን የተላለፈው በእነሱ አለመሆኑን ይናገራሉ፡፡ እነሱ ያደረጉት ነገር፣ የስነምግባር ኮሚቴው ተስማምቶ ያሳላፈውን ውሳኔ ተግባራዊ ማድረግ ብቻ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ የብሄራዊ ምርጫ ኮሚሽኑ የትምህርት መኮንን ቲት ሱ ሙዋንዛሊላ እንዲህ ብለዋል፤

እነዚህ በስነምግባር ኮሚቴው የተወሰዱ እምርጃዎች ናቸው፡፡ የኮሚቴው 90 ከመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተውጣጡ ናቸው፡፡ውሳኔው የተሰጠው የማይሬድ ፖለቲካ ፓርቲንና መንግሥትን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የኮሚሽኑ አባላትን ያካተተ ነው፡፡

እኤአ ባለፈው ማክሰኞ ጥቅምት 1 በታንዛኒያ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴት ስ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ ስለ መጭው ምርጫ ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር እንደማያወግን የትኛውንም ተወዳዳሪም ሆነ ቡድን እንደማይደግፍ አስታውቋል፡፡ ይሁን እንጂ በታንዛኒያ የሚደረገውን ዴሞክራሲያዊ ሂደት እንደሚያግዝና ይህም ደግሞ ነጻን ፍትሃዊ ምርጫ መካሄዱን እንደሚጨምር አስታውቋል፡፡ የአገሪቱ ገዥ ፓርቲም ግለሰቦች በተለይም የፖለቲካ ቡድኖችም ሁሉም ሰው ሂደቱን ቢከታተልና ህጉንም ቢያከብር ምርጫውን ነጻና ፍትሀዊ እንደሚሆን አስታውቋል፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ግን ከዚያ ግብ ለመድረስ ገና ረጅም ርቀት መጓዝ እንደሚያስፈልግ ያምናሉ፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ!

የታንዛኒያው ዕጩ የምርጫ ዘመቻቸውን እንዲያቆሙ ታገዱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:02 0:00


XS
SM
MD
LG