በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታንዛኒያ ውስጥ ብዛት ያላቸው በእስር ላይ ያሉት ተቃዋሚ መሪ ደጋፊዎች ታሰሩ


የቻዴማ መሪውና ሌሎችም የፓርቲው መሪዎች እስር ተከትሎ የተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ
የቻዴማ መሪውና ሌሎችም የፓርቲው መሪዎች እስር ተከትሎ የተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ

ባለፈው ወር የታሰሩት ተቃዋሚ መሪ ፍሪደም ምቦዌ የተመሰረተባቸው የሽብር ወንጀል ክስ ሂደት ለሌላ ጊዜ መቀጠሩን ተከትሎ ደጋፊዎቻቸው ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። አድማ በታኝ ፖሊሶች ብዛት ያላቸው ሰልፈኞች አስረዋል።

የዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ የቻዴማ መሪውና ሌሎችም የፓርቲው መሪዎች የተያዙት ህገ መንግሥታዊ ለውጥ ለመጠየቅ የታቀደው ጉባኤ ከመካሄዱ አስቀድሞ ሲሆን የሃምሳ ዘጠኝ ዓመቱ ምቦዌ ሽብርተኝነት በገንዘብ በመደገፍ እና በማሴር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል። ክሱን ተከትሎ የመብት ቡድኖች እና አንዳንድ ምዕራባውያን ሃገሮች ታንዛኒያ በአዲሱ መሪዋ ስር የዲሞክራሲ ይዞታዋ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ተቃዋሚ መሪው በኢንተርኔት በቪዲዮ አማካይነት ዛሬ ችሎቱ ፊት ሊቀርቡ ቀጠሮ ተይዞ በኢንተርኔት እክል ሳቢያ ለነገ ተላልፏል። ደጋፊዎቻቸው ፍርድ ቤቱ ደጃፍ ወጥተው እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

XS
SM
MD
LG