በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታሊባን የምርጫ አማራጭ ዝግ አይደለም አለ


ፎቶ ፋይል፦ የምርጫ ዘመቻዎችና የምርጫ ሠራተኞች
ፎቶ ፋይል፦ የምርጫ ዘመቻዎችና የምርጫ ሠራተኞች

ታሊባን በአፍጋኒስታን በእስላማዊ ወይም የሸሪያ ህግ ላይ ተመስርቶ የሚቋቋም መንግሥት ለመመስረት ምርጫ የማካሄድን አማራጭ ዝግ እንደማያደርገው የታሊባን ቃል አቀባይ ለቪኦኤ ተናገሩ፡፡

በሁለት አስርት ዓመታት ውጊያ ታሊባን ዴሞክራሲያዊ ምርጫዎችን እስላማዊ አይደለኡም በሚል የምርጫ ዘመቻዎችና የምርጫ ሠራተኞች ሲያጠቃ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ያንን አማራጭ ዝግ እንዳማይደርገው አስታውቋል፡፡

የታሊባን ቃል አቀባይ ሱሃሊ ሻሂን ምርጫ መደረግ አለመደረጉ የሚወሰነው ግን በወደፊቱ ህገመንግሥት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የጊዚያው መንግሥቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚር ካሃን ሙተቂ፣ ባለፈው ማክሰኞ ካቡል ውስጥ ምርጫን አስመልክቶ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ የውጭ መንግሥታት በአፍጋኒስታን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ባይገቡ መልካም ነው ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG