በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታሊባንና ቻይና፣ ዩናይትድ ስቴትስ የአፍጋኒስታንን የአየር ክልል እንዳትጥስ ጠየቁ


ታሊባንና ቻይና ዩናይትድ ስቴትስ በአፍጋኒስታን የአየር ክልል ላይ ድሮኖችን ማብረር እንድታቆም ትናንት ረቡዕ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ሁለቱም በየፊናቸው ባውጡት መግለጫ እንደዚህ ያለው እንቅስቃሴ “የአፍጋኒስታንን ሉዓላዊነት እና በታሊባንና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ቀደም ሲል የተገባውን ስምምነት የሚጥስ ነው፡፡” ብለዋል፡፡

ታሊባን በመግለጫው “በቅርቡ ዩናይትድ ስቴትስ ሁሉንም ዓለም አቀፍ መብቶች፣ ህጎችና፣ እንዲሁም በኳታር ዶሃ ለእስላማዊ ኢምሬት ወይም ታሊባን የገባችውን ቃል እየጣሰች የአፍጋኒስታን የተቀደሰው የአየር ክልል በዩናይትድ ስቴትስ ድሮኖች ሲወረሩ ተመልክተናል፡፡” ብሏል፡፡

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሁዋ ቹን ዪንግ ከቤጂንግ ትናንት ረቡዕ ባወጡት መግለጫ “ዩናይትድ ስቴትስ የአፍጋኒስታንን ሉዐላዊነት ነጻነትና የግዛት አንድነት ከልቧ ማክበር ይኖርበታል” ብለዋል፡፡

አያይዘውም “ከሁሉም በላይ፣ ዩናይትድስቴትስ የወታደራዊ ጣልቃ ገብነትን ልማድ ማስወገድ፣ የራሷን ፍላጎት ሌሎች ላይ መጫንን እና ሰዎችን ወደ ሰቆቃና መከራ የመሚከተውን ነገር መደጋገሟን ማስወገድ አለባት ብለዋል፡፡

ከዋሽንግተን በኩል ይህን አስመልከቶ የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡ ይሁን እንጂ የቻይናና ታሊባን መግለጫዎች የወጡት ግን በቅርቡ የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስቴር ከአፍጋኒስታን ውጭ በመሆን በአፍጋኒስታን የሚገኙ ሽብርተኞችን ለማዋጋት አስፈላጊው ሁሉ ሥልጣን ይኖረዋል በሚል የሰጠውን መግለጫ በመከተል ይመስላል፡፡

የፔንታጎንፕሬስ ዋና ጸሀፊ ጆንከርቢ፣ ባላፈው አርብ ለሪፖርተሮች ሲናገሩ “ይህን አቅማችችን ይዘን ወደፊትም የምንቀጥል ይመስለናል፡፡ የአየር ጥቃቱን አስመልከቶ የተለየ ደንቦች የሉም፡፡

በአሁኑ ሰዓት የአየር ክልሉን ነጻ ስለማድረግ ከታሊባን ጋር ምንም ግልጽ መመዘኛ የለም፡፡ ለወደፊቱም በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከርቀት ሆነን ለምናከናውነው የጸረ ሽብር ዘመቻው የአየር ጥቃት፣ ሊኖር ይችላል ብለን የምንጠብቀው መመዘኛም አይኖርም፡” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG