በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታሊባን አሜሪካውያንን የጫነው አውሮፕላን ካቡልን እንዲለቅ ፈቀደ


በአፍጋኒስታን የታሊባን ባለሥልጣናት እኤአ ነሀሴ 31፣ ዩናዩትድ ስቴትስ ወታደራዊ ዘመቻዋን ካቋረጠች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኳትር ቻርተር አየር መንገድ አፍጋኒስታንን ለቀው የሚወጡ ዜጎችን ከካቡል አውሮፕላን ማረፊያ ይዞ እንዲወጣ ፈቅደዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ የጸጥታ ምክር ቤት ቃል አቀባይ ኤምሊ ሆርኒ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ “ዛሬ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አሜሪካውያንና እና ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸውን ዜጎች በኳታር የቻርተር አውሮፕላን፣ ከሃሚድ ካርዛይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ከአገር የሚወጡትበትን መንገድ አመቻችቷል፡፡ ያ አውሮፕላን በሰላም ኳታር ማረፉንም እናረጋግጣለን” ብለዋል፡፡ ታሊባኖችም የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውና ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው የአፍጋን ዜጎች እንዲወጡ በጎ ትብብር ማሳየታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሮይተርስና አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገቡት የኳታር አውሮፕላን 113 ሰዎች የያዘ ሲሆን ከእነዚያ ውስጥ 21 የሚሆኑ አሜሪካውያን፣ 43 ካናዳውያንና 13 የደች ዜግነት ያላቸው መሆኑን የየአገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቃቸውን አመልክተዋል፡፡

በዚህ ሳምንት መግቢያ ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንተኒ ብሊነክንና የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስተን በኳታር ተገኘተው በዚሁ ጉዳይ ላይ መነጋገራቸው ይታወሳል፡፡ ብሊንከን ታሊባን አገር ለቀው መውጣት የሚፈልጉ አሜሪካውያንና ሌሎች ዜጎችን እንዲፈቅድ ያሳሰቡትም በዚሁ ሳምንት መሆኑን ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG