በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በታይዋን አነስተኛው ድምፅ መስጠት የሚያስችል ዕድሜ ወደ 18 ዓመት ዝቅ የማድረግ እንቅስቃሴ


ፎቶ ፋይል፦ የታይዋን ፕሬዚዳንት ሳይ ሊን ዌን፣ በምርጫ ወቅት በታይዋን ኒው ታይፔ ከተማ በሚገኝ የምርጫ ጣቢያ ድምጽ ሰጥተዋል። እኤአ ጃንዋሪ 11/2020
ፎቶ ፋይል፦ የታይዋን ፕሬዚዳንት ሳይ ሊን ዌን፣ በምርጫ ወቅት በታይዋን ኒው ታይፔ ከተማ በሚገኝ የምርጫ ጣቢያ ድምጽ ሰጥተዋል። እኤአ ጃንዋሪ 11/2020

ዕድሜያቸው 18 ዓመት የሞላ ታይዋናውያን ራሳቸውን ችለው ሊኖሩ፣ ትዳር ሊመሰርቱ አለያም ቢከሰሱ አዋቂዎች በሚበየኑበት የሕግ አግባብ ፍርድ ቤት ቀርበው ሊጠየቁ እና ለውትድርና አገልግሎት ሊጠሩ ጭምር ይችላሉ። ይሁንና በፕሬዚዳንታዊ እና የሕግ አውጭዎች ምርጫ ድምፅ መስጠት አይችሉም።

ለዓመታት ውይይት ቢደረግበት እና 18 ዓመት የሞላቸውን ወጣቶችን መብት ለማስከበር የተቀየሰ ጥረት በእጅጉ በማዝገሙ፤ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ከመጣ ከሩብ ምዕተ-ዓመት በኋላም በታይዋን በብሄራዊ ደረጃ ድምፅ መስጠት የሚያስችለው ዕድሜ ከሃያ ዓመት ዝቅ ሳይል ቀርቷል።.

እኤአ ከ2017 ጀምሮ፣ ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የታይዋን ዜጎች በብሔራዊ ደረጃ በሚካሄዱ ህዝበ ውሳኔዎች ድምፅ መስጠት ይችላሉ። በተጨማሪም በ2023ዓም 18 ዓመት የሞላው የታይዋን ወጣት በዕድሜው እርከን እንደ አዋቂ መቆጠር ይጀምራል። የባንክ ብድር የማግኘት፣ ክሬዲት ካርድ የመጠቀም እና የኪራይ ውል የመፈጸም መብት ስለሚጎናጸፍ ራስን በራስ የማስተዳደር የፋይናንስ ነጻነት ምብት የሚያጎናጽፍ በር ይከፈትላቸዋል።

በአንፃሩም ፕሬዚዳንታቸውን እና ተወካዮቻቸውን መምረጥ ይችሉ እንደሆን፣ መደረግ ያለበት ሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያ ዋና ዋና የሚባሉትን መሰናክሎች ማለፍ በመቻል ያለመቻሉ ይወሰናል።

ለዚህም እንደ ብርቱ ፈተና ከሚታዩትም ውስጥ አሁንም የ18 እና 19 ዓመት ዕድሜ ያላቸውን ወጣቶች በፖለቲካዊ እንዳልበሰሉ ጨቅላ አድርገው የሚመለከቱ ወግ አጥባቂ ማኅበራዊ አመለካከቶች ናቸው። በመሆኑም ጥረቱ ታይዋንን ጨምሮ በመላው ቻይና የሚንቀሳቀሰው እና (በታይዋን ትልቁ ከሆነው) “ኮመንቴ” ወይም “የቻይና ብሔራዊ ፓርቲ” በመባል ከሚታወቀው ፓርቲ ተቃውሞ ገጥሞታል።

የማሻሻያ ሕጉ ደጋፊዎች ደግሞ - ሁለቱም በወጣት መራጮች ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍ ያላቸው - ገዥው መሃል ግራ-ዘመም ዲሞክራሲያዊ ሕዝቦች ፓርቲ እና የመሃል ግራ ዘመሙ አዲሱ ፓወር ፓርቲ - እንዲሁም ማዕከላዊው የታይዋን ህዝቦች ፓርቲ ናቸው።

በታይዋን ድምፅ መስጠት የሚያስችለውን ዕድሜን ዝቅ ለማድረግ ያለው የህዝብ ድጋፍ ውጤት በአመዛኙ የፓርቲ መስመርን የተከተለ ነው።

XS
SM
MD
LG