በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታይዋን ከዩናይትድ ስቴትስ የምትገዛው የጸረ ባህረ ሰርጓጅ ሂሊኮፕተር ተወደደብኝ አለች


ፎቶ ፋይል፦ የታይዋን ወታደሮች በአሜሪካ የተሰራ ባለሁለት mount Stinger ሚሳይል ሲያሳዩ እአአ ነሐሴ 11/2005
ፎቶ ፋይል፦ የታይዋን ወታደሮች በአሜሪካ የተሰራ ባለሁለት mount Stinger ሚሳይል ሲያሳዩ እአአ ነሐሴ 11/2005

ታይዋን ዛሬ ሀሙስ በሰጠቸው መግለጫ፣ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የጸረ ባህር ሰርጓጅ የጦር ሂሊኮፕተሮችን፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ለመግዛት ያቀደችውን ፕላን፣ መሳሪያዎቹ እጅግ ውድ ናቸው በሚል ምክንያት ለመሰረዝ ማሰቧን፣ ፍንጭ ሰጥታለች፡፡

ታዋይን ቀደም ሲል 12 MH-60R የተባሉ የጸረ ባህር ሰርጓጅ የጦር ሂሊኮፕተሮችን ለመግዛት አቅዳ እንደነበረ ተገልጿል፡፡

የታይዋን መከላከያ ሚኒስትር ቺሁ ኩዎ ቼንግ በታይዋን ምክር ቤት ስለ ግዥው ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፣

“ዋጋው እጅግ ውድና ከአገሪቱ አቅም በላይ ነው” ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ የታዋይን ፕሬዚዳንት ዛይ ሊንግ እጅግ የተራቀቁ በከፍተኛ ደረጃ መንቀሳቀስ የሚችሉና በቀላሉ የማይደመሰሱ፣ ኢላማቸው በትክክል መምታት የሚችሉ የጦር መሳሪያዎችን የመታጠቅ ሀሳብ በማራማመድ የሚታወቁ መሆኑን ተነገሯል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ከቻይና ጥቃት የሚሰነዝርባት ቢሆን፣ ታይዋን ከወዲሁ ራሷን በዘመናዊ መሳሪያ አደራጅታ እንድትጠብቅ የምትገፋፋ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG