በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የውጭ ጉዳዬ ቻይናን አያገባትም” - ታይዋን


ጆሴፍ ዉ
ጆሴፍ ዉ

ታይዋን ሌሎችም የውጭ ልዑካን ቡድኖችን በደስታ እንደምትቀበልና በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ ናንሲ ፐሎሲ ጉብኝት በተበሳጨችው ቻይና የቁጣ ምላሽ እንደማትሸበረክ የውጭ ጉዳይሚኒስትሯ ጆሴፍ ዉ አስታወቁ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዛሬ ዐርብ በተለይ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ለፐሎሲ ጉብኝት አፀፋ የተካሄዱትን የቻይናን ወታደራዊ ልምምዶች ተችተዋል።

ቤጂንግን በታይዋን የባህር ወሽመጥ ላይ “የነበረውን ሁኔታ አበላሽታለች” ሲሉ ሚኒስትሩ ከስሰዋል።

የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ ነገር ቻይናን አይመከታትም ሲሉ ሚኒስትሩ አክለው ተናግረዋል።

“ትክከለኛውን ነገር የምናደርግ ከሆነ የቻይና ቁጣ ሊያቆመን እንደማይችል ልናስታውስ ይገባናል” ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዉ “ታይዋይንን ሁልጊዜም በወታደራዊ ኃይል ለማስፈራራት ሰበብ አያጡም” ሲሉ አክለዋል።

ከፐሎሲ ጉብኝት በኋላ ቻይና ታይዋንን ለበርካታ ቀናት ከብባ ታይቶ የማያውቅ ግዙፍ ወታደራዊ ልምምድ አድርጋለች።

ልምምዱን ደሴቲቱን ከተቀረው ዓለም ለመነጠል ወይም ለመውረር የሚካሄድ ልምምድ አድርገው የቻይና መገናኛ ብዙኃን እንደሚገልፁት ተዘግቧል።

XS
SM
MD
LG