በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ተቃውሞ ለ11ኛ ጊዜ ቀጥሏል ሰልፈኞች በአስለቃሽ ጋዝ ተበተኑ


በሱዳን ወታደራዊ ቡድን የተካሄደውን መፈንቀለ መንግሥት በመቃወም የወጡት ሰልፈኞች
በሱዳን ወታደራዊ ቡድን የተካሄደውን መፈንቀለ መንግሥት በመቃወም የወጡት ሰልፈኞች

ዛሬ በሱዳን ለ11ኛ ጊዜ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ወደ ቤተመንግሥቱ ያመሩ የነበሩ ሰልፈኞችን ለመበተን የሱዳን ጸጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጋዝ መጠቀማቸውን ሮይተርስ የዓይን እማኞችን ጠቅሶ ዘገበ፡፡

ባላፈው ጥቅምት በሱዳን ወታደራዊ ቡድን የተካሄደውን መፈንቀለ መንግሥት በመቃወም የወጡት ሰልፈኞች ወታደራዊ ቡድኑ በሱዳን የፖለቲካ ሽግግርም ሆነ በሚካሄደው ነጻ ምርጫ ምንም ስፍራ የለውም የሚል ተቃውሟቸውን ማሰማታቸውን ቀጥለዋል፡፡

ባላፈው ቅዳሜም ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ የተካሄደ መሆኑን ሲገለጽ ከሱዳን የጸጥታ ኃይሎች ተመሳሳይ ጥቃት የተፈጸመባቸው መሆኑን ተመልክቷል፡፡

የዛሬን ተቃውሞ ተክትሎ በካርቱም የኢንተርኔትና የሞባይል ስልክ አገልግሎት የተቋረጠ መሆኑን ተዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG