በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት የብሉ ናይል ክፍለ ግዛት የጦር አዛዥ አነሳ


ሱዳን
ሱዳን

የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ሁለት ቀናት በዘለቀውና ቢያንስ 220 ሰዎች የሞቱበትን ከባድ የጎሳዎች ግጭት ተከትሎ የደቡባዊዋን ብሉ ናይል ክፍለ ግዛት የጦር አዛዥን ከሥልጣናቸው ማንሳቱ ተነገረ፡፡

ከኢትዮጵያ እና ከደቡብ ሱዳንን ጋር በምትዋሰነው በብሉ ናይል ክፍለ ግዛት በሀውሳ እና በርታ ጎሳዎች መካከል ባገረሸው ብጥብጥ በርስ በርስ ግጭት ውስጥ የምትገኘውን አገር የፖለቲካ ቀውስ እንዳበዛው ተመልክቷል፡፡

በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ዋድ ኤል ማሂ ከተማ ውስጥ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ እና ሀሙስ ውጥረት ተባብሶ እንደነበርም ተገልጿል፡፡

ግጭቱ የተከሰተው በሀገሪቱ ለአጭር ጊዜ ታይቶ የነበረውን የዴሞክራሲ ሽግግር የሱዳን ወታደራዊ ግልበጣ ባስተጓጎለበት አንደኛ ዓመት ላይ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

ጠንካራው ወታደራዊ መንግሥት በክፍለ ግዛቱ የሚገኙ የብሄረሰብ ቡድኖችን ደህንነት መከላከል አልቻለም የሚል ትችት እየተሰነዘረበት መሆኑ በአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ ተመልክቷል፡፡

ከስልጣናቸው በተነሱት በሜጀር ጄኔራል ራምዚ ባባካር ምትክ ሚጀር ጄኔራል ራቤይ አብደላ አደም የብሉ ናይል የጦር ኃይል አዛዥ ሆነው መሾማቸውን የሱዳን የጦር ኃይል ቃል አቀባይ አስታውቀዋል፡፡

ሹም ሽሩ የተከናወነዉ አሳዛኝ ለሆኑ የጸጥታ ሁኒታዎች መፍትሄ ለመፈለግ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ ግጭቶቹን የሚመረምር ተልዕኮም ተመሥርቷል ብለዋል፡፡

የብሉ ናይል የጤና ሚኒስቴር ሹም ፋት አራህማን ባኺት ትናንት ዕሁድ በሰጡት መግለጫ የመጀመሪያው የሰብዐዊ እርዳታ እና የሀኪሞች ቡድን ቅዳሜ ማታ ዋድ አል ማሂ ከተማ ከደረሰ በኋላ ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ ሊታወቅ መቻሉን አመልክተዋል፡፡

የክፍለ ሀገሩ ባለሥልጣናት የሌሊት የሰዓት ዕላፊ ያወጁ ሲሆን ሁከቱ እንዳይቀጥል ለመከላከል ተጨማሪ ኃይል አሰማርተዋል፡፡

በክፍለ ሀገሯ መዲና ዳማዚን ግጭቱ ያስቆጣቸው ተቃዋሚ ሰልፈኞች ትናንት እሁድ የክፍለ ሀገሩን የአስተዳደር እና የጦር ኃይል መሥሪያ ቤቶች ጥሰው መግባታቸውን የአገር ውስጥ የዜና ማሰራጫዎች ዘግበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG