በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምዕራብ ዳርፉር ፀጥታ አስተማማኝ እንዳልሆነ ተገለጠ


በሱዳን ምዕራብ ዳርፉር ክፍለ ግዛት
በሱዳን ምዕራብ ዳርፉር ክፍለ ግዛት

በሱዳን ምዕራብ ዳርፉር ክፍለ ግዛት ከተቀሰቀሰው አስራ ዘጠኝ ሰዎች የተገደሉበት ሁከት በኋላ አካባቢው የተረጋጋ ቢሆንም የፀጥታው ሁኔታ አሁንም የማያስተማምን መሆኑን አንድ ተፈናቃዮችን እና ስደተኞችን የሚረዳ ነፃ ድርጅት አሳሰበ።

የዳርፉር ስደተኞች እና የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ድጋፍ አስተባባሪ ቡድን ቃል አቀባይ አዳም ራጂል ለቪኦኤ የደቡብ ሱዳን ትኩረት ክፍል በሰጡት ቃል ዳርፉር እና በተለይ ደግሞ ጀበል ሙን አካባቢ የሀገሪቱ ወታደራዊ መንግሥት የጦር ኃይል እያየ ባልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎች ሚሊሽያዎች ጥቃት እያደረሱ ናቸው ብለዋል።

የሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ እንዳስታወቀው ቅዳሜ ዕለት ጀበል ሙን ውስጥ ሚሊሽያዎች በሲቪሎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ሠላሳ አምስት ደርሷል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሱዳን የተቀናጀ የሽግግር ድጋፍ ተልዕኮ ተጠሪው ቮልከር ፕርት ጥቃቱን አውግዘዋል።

የመንግሥቱ ሉዓላዊ ምክር ቤት ቃል አቀባይ አብደልጃባር አልሙባራክ ሙሳ ትናንት ሰኞ በሰጡት ቃል ሲቪሎችን ከጥቃት መጠበቅና ዳርፉርን ማረጋጊያ ዕቅድ አገራዊ ዕቅድ እንደሚያስፈልግ ውይይት ተካሂዷል ብለዋል።

እአአ በ2020 በሱዳን የሽግግር መንግሥት እና በዳርፉር አማጽያን መካከል በተደረሰው የሰላም ሥምምነት ሰላማዊ ሰዎችን ከጥቃት የሚጠብቅ ልዩ ኃይል ለማቋቋም የታቀደ ቢሆንም እስካሁን ተግባራዊ አልሆነም።

XS
SM
MD
LG