በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ጦርነት ሰላማዊ ዜጎችን አጣብቂኝ ውስጥ ከቷቸዋል


ፎቶ ፋይል፡ ካርቱም፣ ሱዳን
ፎቶ ፋይል፡ ካርቱም፣ ሱዳን

የተኩስ ማቆም ስምምነቱ ማብቃቱን ተከትሎ፣ በሱዳን ዋና ከተማ፣ በተፋላሚ ወገኖች መካከል የሚካሄደው ውጊያ ሰኞ እለት ተባብሶ ቀጥሎ የአየር ድብደባ፣ መድፍ እና የተኩስ ልውውጥ የተካሄደ ሲሆን፣ ንፁሃን ዜጎች እየከፋ በሄደው ሰብዓዊ ቀውስ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል።

በሀገሪቱ ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች መካከል በጅዳ የተካሄደው ንግግር ጦርነቱን ማስቆም ሳይችል በመቅረቱ፣ የተኩስ ማቆም ስምምነቱ እሁድ እለት እንዳበቃ ውጊያው ቀጥሏል።

ሁለት ወራት ባስቆጠረው ጦርነት ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በመዲናዋ መስፋፋት፣ መንገዶችን መቆጣጠር እና በአንዳንድ መኖሪያ ቤቶች ካምፕ ማቋቋም ቢችሉም፣ የሀገሪቱ ጦር በአየር እና መድፍ መሳሪያዎች የበላይነት አለው።

የምስራቅ ካርቱም ነዋሪዎች የአየር ድብደባ እንደደረሰባቸው ሲገልፁ፣ የደቡብ ካርቱም እና የሰሜናዊ ኦምዱርማን ከተማ ነዋሪዎች ደግሞ የመድፍ ውጊያ መካሄዱን ተናግረዋል። በማዕከላዊ ካርቱምም እንዲሁ ውጊያ መካሄዱን የአይን እማኞች አመልክተዋል።

ጦርነቱ እስካሁን ወደ 2 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎችን እንዲሰደዱ ከማድረጉ በተጨማሪ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲወደም እና የኤሌትሪክ እና የውሃ መቆራረጥ እንዲደፈጠር አድርጓል። ከሀገር መውጣት ያልቻሉት ደግሞ፣ መንግስት ደሞዝ እና ጡረታ መክፈል በማቆሙ ችግር ላይ ወድቀዋል።

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ሰኞ እለት በሰጡት መግለጫ፣ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ አመራሮች ጋር በአስር ቀናት ውስጥ ፊት ለፊት እንደሚገናኙ እና፣ ጦርነቱን ማስቆም እና ሰብዓዊ ኮሪደሮችን መክፈት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ እንደሚወያዩ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG