በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ተፋላሚዎች ወደ መነጋገር እንዲመጡ ተመድ በድጋሚ ጠየቀ


ካርቱም፤ ሱዳን
ካርቱም፤ ሱዳን

በሱዳን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካይ፣ በአገሪቱ በመፋለም ላይ ያሉት ሁለቱ ወገኖች፣ ውጊያውን አቁመው ወደ ሐቀኛ ውይይት እንዲገቡ በድጋሚ ጥሪ አድርገዋል፡፡

ውጊያው እየተጠናከረ በመምጣቱ፣ ካርቱምን ለቅቀው ወደ ፖርት ሱዳን የሔዱት ቮልከር ፐርዝስ፥ የአገሪቱ ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ወኪሎች፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በሌላ አገር በአካል ተገናኝተው እንዲነጋገሩ ለማድረግ ጥረት በመደረግ ላይ ነው፤ ብለዋል፡፡

በሱዳን የተመድ የሽግግር እገዛ ልዑክ መሪ የኾኑት ፐርዝስ፣ ሁለቱን ወገኖች በተደጋጋሚ በማነጋገር ላይ እንደኾኑ አስታውቀዋል፡፡

ወደ ግጭት ያመራውን ቅራኔ ለመፍታት ብቸኛው መፍትሔ፣ ውይይት መኾኑን ፐርዝስ ተናግረዋል፡፡

በደረሰባቸው ጥቃት፣ በአቅርቦት እና በሠራተኛ እጥረት፣ እንዲሁም በውሃ እና መብራት አለመኖር ብዙዎቹ ሆስፒታሎች ተዘግተዋል፡፡

ጥቂት የማይባሉ የረድኤት ድርጅቶች፣ ሥራቸውን በማቆም ሠራተኞቻቸውን ከሱዳን በማስወጣታቸው፣ የሰብአዊ ተራድኦ ኹኔታዎች እየተዳከሙ እና እየተመናመኑ መሔዳቸውን ቀጥለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG