በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ስለ ሱዳን ሰላም በሚመክረው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ካይሮ ገብተዋል


የኤርትራው ፕሬዚዳንት ስለ ሱዳን ሰላም በሚመክረው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ካይሮ ገብተዋል
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ስለ ሱዳን ሰላም በሚመክረው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ካይሮ ገብተዋል

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈ ወርቂ፣ በሱዳን ግጭት ጉዳይ፣ ነገ በግብጽ ለሚደረገው የጎረቤት ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ካይሮ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈ ወርቂ፣ ሌሎች ባለሥልጣኖቻቸውንም ይዘው እንደተጓዙ፣ የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።

ባለፈው ሰኞ፣ አራት አባላት ያሉት የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ቡድን(IGAD)፣ በሱዳኑ ግጭት ላይ ለመነጋገር በዐዲስ አበባ ተስብሰቦ የነበረ ሲኾን፣ ሁለቱም ተፋላሚ ጄኔራሎች በስብሰባው ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል።

በዐዲስ አበባ የተካሔደውን ስብሰባ፣ ኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ መምራት የለባቸውም፤ ለተቃዋሚው ኃይል ያደላሉ፤”

“በዐዲስ አበባ የተካሔደውን ስብሰባ፣ ኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ መምራት የለባቸውም፤ ለተቃዋሚው ኃይል ያደላሉ፤” በሚል፣ የሱዳን መንግሥት በስብሰባው እንደማይሳተፍ አስታውቆ ነበር። ተቀናቃኙ የፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኃይሉ፣ አንድ ተወካዩ በስብሰባው ላይ እንዲገኝ ወደ ዐዲስ አበባ ልኮ ነበር።

በአሜሪካ እና በሳዑዲ አረቢያ አሸማጋይነት፣ ሁለቱን ወገኖች ስምምነት ላይ ለማድረስ፣ ባለፈው ወር ለሳምንታት ሲደረግ የነበረው ጥረት ሳይሳካ መቅረቱ ይታወሳል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG