በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ሽግግር መንግሥት የሰላም ሥምምነት ተፈራረመ


የሱዳን የሽግግር መንግሥት በግጭት በሚታመሰው በምዕራብ ዳርፉር ግዛት ከሚንቀሳቀሱ አማጺ ቡድኖች ጋር የሰላም ሥምምነት ላይ መድረሱ ተገለጠ።

ስምምነቱ ከሰባት ዓመታት በፊት ከሱዳን በተገነጠለችው በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ዛሬ መፈረሙን የሽግግሩ የሥልጣን ክፍፍል መንግሥት አስታውቋል።

ሥምምነቱ የተደረሰው የፍትህ እና የዕኩልነት ንቅናቄ እና የሱዳን ነጻ አውጪ የጦር ሰራዊትን ከሚያቅፈው የሱዳን አብዮታዊ ግንባር ጋር መሆኑንም አመልክቷል።

ግንባሩ በአጎራባቾቹ ደቡብ ኮርዶፋን እና ብሉ ናይል ክፍለ ግዛቶች የተዋጉ አማጺ ቡድኖችንም ያካተተ ነው።

በደቡብ ሱዳን ሽምግልና የተደረሰው ስምምነት ለአማጺ ቡድኖቹ የፖለቲካ ውክልና እንዲኖራቸው፣ ተዋጊዎቻቸው በብሄራዊ የፀጥታ ኃይሉ እንዲዋሃዱ የኢኮኖሚና የመሬት ይዞታ መብታቸውም የሚረጋገጥበት እንደሚሆን ተጠቁሟል። ስምምነቱን አንፈርምም ያሉ ሁለት አማጺ ቡድኖች መኖራቸውም ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG