በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትናንቱ የሱዳን ተቃውሞ ጸጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጋዝ ተጠቀሙ


በዋና ከተማይቱ ካርቱም ተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ
በዋና ከተማይቱ ካርቱም ተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ

በሱዳን ትናንት ሀሙስ ቀጥሎ የዋለውን የተቃውሞ ሰልፍ ለመበተን የሱዳን ጸጥታ ኃይሎች ተቀጣጣይ መሳሪያዎችንና የአስለቃሽ ጋዝ መጠቀማቸውን የዴሞክራሲ ደጋፊ ተቃዋሚዎች አስታውቁ፡፡

በካርቱም እና በምዕራብ የሱዳን ክፍለ ግዛት በምትገኘው ዳርፉር በተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች 6 ሰዎች መቁሰላቸው ተገልጿል፡፡

ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከተካሄደ እስካሁን ድረስ 63 ሰዎች መገደላቸውና በመቶዎች የሚቆጠሩ መቁሰላቸውን የህክምና ቡድን አባላት አስታውቀዋል፡፡

ተቃዋሚዎቹ የሱዳን ወታደራዊ መሪዎች ከሥልጣን ተወግደው የሲቪል መንግሥት የሚመራ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም የሚጠይቁ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የተባበሩት መንግሥት ካላፈው ሰኞ ጀምሮ በሁሉም የፖለቲካ ቡድኖች መካከል ንግግር እንዲኖር ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

መንግሥት አልባ በመሰለቸው ሱዳን፣ የውጭ እርዳታ መቋረጡ ተነገሯል፡፡

በ10ሺዎ የሚቆጠሩ ሰዎች ተቃውሟቸውን በእየለቱ የሚያካሂዱባት አገር ስትመስል፣ በተቃዋሚዎቹ ላይ የሚደርሰውም ጥቃትም በዚያው መጠን መቀጠሉ ይስተዋላል፡፡

XS
SM
MD
LG