ዋሽንግተን ዲሲ —
በሱዳን በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች፣ ባላፈው ጥቅምት መፈንቅለ መንግሥት ባካሄዱት ወታደራዊ መንግሥት አመራሮች ላይ የሚያሳድሩትን ጫና በመቀጠል፣ ትናንት ሰኞም በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡
ከግልበጣው በኋላ በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ወታደራዊ መሪዎቹ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክን ወደ ሥልጣናቸው የመለሱ መሆኑን ቢገልጹም ሱዳንውያን ግን አሁንም በተቃውሟቸው የገፉበት መሆኑን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል፡፡