በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር የደቡብ ሱዳን ጁባ ጉብኝት


የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ
የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በአጎራባች ደቡብ ሱዳን ጉብኝት አድርገዋል። ለሁለት ቀን ጉብኝት ትናንት ጁባ የገቡት፣ የደቡብ ሱዳን ሰላም ጥረት መጠናከር ስለሚችልበት መንገድ ለመነጋገር መሆኑ ተገልጿል።

ሃምዶክ የተጓዙት የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሪያክ ማቻር የሚመሩት ኤስፒኤልኤም/ኤ አይኦ ተብሎ የሚጠራው የደቡብ ሱዳን ነጻ አውጭ ንቅናቄ ተቃዋሚ አንጃ በውስጥ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ በሚገኝበት ባሁኑ ወቅት መሆኑ ነው።

የካርቱም እና የጁባ ባለሥልጣናት ስለሀገሮቻቸው ግንኙነት እንደሚወያዩ ይጠበቃል። ከዚያም በተጨማሪ ባለፈው ዓመት የሱዳን የሽግግር መንግሥት በሀገሪቱ ከሚንቀሳቀሱ በርካታ ታጣቂ ቡድኖች ጋር ጁባ ላይ ስለተፈራረመው የሰላም ውል ተግባራዊነትም ያነሳሉ ተብሏል።

ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዶክ ጋር ወደ ጁባ የተጓዙት የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርያም አል ማህዲ የደቡብ ሱዳ የሰላም ውል ተግባራዊነት መጓተቱ የሀገራችንን አመራር አሳስቧል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዶክ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር፣ ከምክትል ፕሬዚዳንቱ ማቻር ከሌሎችም የፖለቲካ መሪዎች ጋር ይነጋገራሉ።

እንዲሁም ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታንያ እና ኖርዌይ ዲፕሎማቶችም ጋር እንደሚነጋገሩ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG