በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ውጊያውን ሸሽተው ወደሱዳን የሚሰደዱ ቁጥራቸው እየጨመረ ነው - ተመድ


በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውጊያውን ሸሽተው ወደሱዳን የተሰደዱ
በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውጊያውን ሸሽተው ወደሱዳን የተሰደዱ

የሰብዓዊ ረድዔት ድርጅቶች በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውጊያውን ሸሽተው ወደሱዳን መግባታቸውን የቀጠሉትን ስደተኞች ለመርዳት ጥረታቸውን እያጠናከሩ መሆናቸውን ገለጽ።

በሱዳን የተመድ የስደተኞች ኮሚሽን የአጣዳፊ እርዳታ አስተባባሪ ዬንስ ሄሰማን በየቀኑ በሽዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ድንበር አቋርጠው ሱዳን እየገቡ ነው ብሏል።

የዩኤንኤችሲአር የስደተኛ ተቀባይ ሰራተኞች እስካሁን ከአርባ ሽህ በላይ ኢትዮጵያውያን መመዝገባቸውን ገልጿል።

ስደተኞቹ ድንበር የሚያቋርጡት በሱዳን ከሰላ ክፍለ ግዛት ሃምዲያት፣ በገዳሪፍ ክፍለ ግዛት በሉግዲ የድንበር ኬላዎች በኩል መሆኑን፤ በሌላኛው በደቡቡ አቅጣጫ በአደራፊ በኩል መግባት ጀምረዋል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ሰባት መቶ የሚሆኑ ገብተዋል ብሏል።

ውጊያው ከቀጠለ የሚሰደደው ሰው ቁጥር ፈጥኖ ሁለት መቶ ሽህ ሊደርስ እንደሚችል የተመድ ባለሥልጣን አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG