በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ባለሥልጣናት ሁለት የቀድሞ ባለሥልጣናትን ከአስር ለቀቁ


የሱዳን ባለሥልጣናት በአስር ላይ የነበሩ ሁለት የቀደሞ መንግሥት ባለሥልጣናትን መልቀቃቸውን ጠበቆቻቸው ገለጹ። ለሦላሳ ዓመታት በአምባገነኑ የኦመር አል በሲር አእገዛዝ ስር በነበረችው በሱዳን ተጀምሮ የነበረውን የዲሞክራሲ ሽግግር የጦር ሰራዊቱ መቀልበሱን ተከትሎ በሀገሪቱ የነገሰውን የፖለቲካ አጣብቂኝ ለመፍታት ጥረት አየተደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ፊት ለፊት በመናገር የሚታወቁትን የቀድሞዎቹን ባለሥልጣናት የፈታቸው ትምምን ለመገንባት ነው ተብሏል።

የቀድሞ የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትሩ ካሊድ ኦመር ማክሰኞ ማታ የተለቀቁ ሲሆን የቀድሞው የገዢው ሉዐላዊ ምክር ቤት አእባል የነበሩት መሃመድ አእል ፋኪ ደግሞ ትናንት ማታ መፈታታቸውን ጠበቆቻቸው ገልጸዋል።

ሁለቱ ባለሥልጣናት የጥቅምቱን የመንግሥት ግልበጣ ተከትሎ ከሌሎች በርካታ የቀድሞ ባለሥልጣናት ጋር ታስረው የጦር ሰራዊቱ አና ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ባደረጉት ሥምምነት ከአንድ ወር በኋላ ተለቅቀው ነበር።

በጄኔራሎቹ አና በተቃዋሚ ንቅናቄው መካከል ልዩነቱን ለማጥበብ ባለመቻሉ ሃምዶክ በጥር ወር ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን ተከትሎ ነበር ሁለቱ ባለሥልጣናት አንደገና የታሰሩት።

XS
SM
MD
LG