በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ግጭት የለስላሳ መጠጥ ግብአት እጥረት አስከተለ


በሱዳን እየተካሔደ ያለው ግጭት፣ በዓለም አቀፍ አምራቾች፥ ለለስላሳ መጠጥ፣ ለከረሜላ እና ለመዋቢያዎች ግብአት የሚውለውንና ገም አራቢክ የተሰኘው ንጥረ ነገር እጥረት ማስከተሉ ተገለጸ፡፡

በዓለም 70 በመቶ የሚኾነው ገም አራቢክ የሚገኘው፣ በአፍሪካ በቆዳ ስፋቷ ሦስተኛ ከኾነችው ሱዳን ነው፡፡ የአኬሺያ ዛፎች ተዋፅኦ የኾነውን ገም አራቢክን ሊተኩ የሚችሉ ንጥረ ነገሮች፣ በጣም ጥቂት መኾናቸውን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ገም አራቢክ የለስላሳ መጠጥ ግብአት፣ በዓመት እስከ 1ነጥብ1 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገቢ ያስገኛል፡፡ በረሓማው የአየር ንብረት እና የእህል ምርት የሚያመርተው ክልል የሚጋጠሙበት፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ አፍሪካ የተዘረጋው አካባቢ “የገም ቀለበት” ተብሎ ይጠራል፡፡

ኢትዮጵያ፣ ቻድ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ በዚኹ ቀለበት ይካለላሉ፡፡ ገም አራቢክ፣ ለዓለም ገበያ እጅግ አስፈላጊ በመኾኑ፣ በሱዳን ላይ ለዐሥርት ዓመታት ተጥሎ በቆየው ማዕቀብ ዝርዝር ውስጥ አልተካተተም ነበር፡፡ ይህም፣ የንጥረ ነገሩን ሕገ ወጥ ንግድ ለመቋቋም እንደነበር ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG