በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ውጊያ ቻይና በገለልተኝነት ጥቅሟን ማራመድን መምረጧ ተገለጸ


በሱዳን ውጊያ ቻይና በገለልተኝነት ጥቅሟን ማራመድን መምረጧ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:02 0:00

በሱዳን ውጊያ ቻይና በገለልተኝነት ጥቅሟን ማራመድን መምረጧ ተገለጸ

ቻይና፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ በሱዳን የኤነርጂ፣ የግብርና እና የትራንስፖርት ዘርፎች፣ ከፍተኛ የኢንቬስትመንት አጋርነት ተሳትፎ ስታደርግ ቆይታለች፡፡ ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ በእነኚኽ ዘርፎች፣ ወደ ስድስት ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ሙዓለ ነዋይ አፍስሳለች፡፡

ቻይና፣ ከሱዳን ጋራ ያላት የጥቅም ትስስር፣ በ1950ዎቹ የጀመረ ቢኾንም፣ ግንኙነታቸው እየሠመረ እና እየጎላ የሔደው ግን፣ ዩናይትድ ስቴትስ በ1990 በሱዳን ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ከጣለች በኋላ ነው፡፡

ዛሬ ፍልሚያ ላይ ያሉት የሱዳን ኀይሎች፣ ሊረጋ ያልቻለውን የተኩስ አቁም ውላቸውን ዕድሜ እንዲያራዝሙ፣ ልዩ ልዩ ሀገራት ጥረት እያደረጉ ባሉበት በአሁኑ ወቅት፣ ቻይና ከነገሩ ሁሉ ጦመኛ ኾና ገለልተኛ አቋም በመያዝ የራሷን ጥቅም ማራመድን እንደመረጠች፣ ኹኔታውን የሚከታተሉ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡

ኤድዋርድ ዪራኒያን ከካይሮ ለቪኦኤ ያጠናቀረው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፡፡ ቆንጅት ታየ ታቀርበዋለች፡፡

XS
SM
MD
LG