በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ በሱዳን ዴሞክራሲ አደጋ ላይ ነው አለ


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ያወጣው አንድ ሪፖርት ባለፈው ጥቅምት በሱዳን የተካሄደው መፈንቀለ መንግሥት በአገሪቱ የዴሞክራሲ ጅምር ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ መሆኑንና ምናልባትም ሊቀለበስ ከማይችልበት ደረጃ ሊደርስ እንደሚችል አመለከተ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት ወታደራዊ መፈቅለ መንግሥቱ ሱዳንን ትልቅ ቀውስ የከተታት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከመፈንቅለ መንግሥቱ ወዲህም በሱዳን ዘርፈ ብዙ የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈጸሙንና በሺህዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያንም መብታቸውን ለማስከበር ለተቃውሞ ወደ አደባባይ መውጣታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንዲህ አሉ ኮሚሽነሯ

“በዚያ መጠንም በፀጥታው ኃይሎች የሚወሰደው መጠን ያለፈው ተደጋጋሚ የኃይል እምርጃ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ አውቶማቲክ የቡድንና የነፍስ ወከፍ የተኩስ መሳሪያዎቻቸውንም በተቃዋሚዎች ላይ በቀጥታ እየተጠቀሙ ነው፡፡ አስለቃሽ መሳሪያዎችን ወደ ሰዎች ጭንቅላትና አካል ላይ በመተኮስ ዓለም አቀፉን ህግ በግልጽ እየጣሱ ነው፡፡’’

ሪፖርቱ በሆስፒታሎች፣ በጤና ተቋማትና፣ የጤና ሠራተኞችን ጨምሮ በፀጥታ ኃይሎች የተፈጸሙ በርካታ ጥቃትና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በዝርዝር መያዙ ተነግሯል፡፡ በዘፈቀደ ስለሚታሰሩ ሰዎችና ኢላማ የተደረጉ ተቃዋሚችና ድጅቶች መኖራቸውንም ያመለካተ መሆኑ ገልጿል፡፡ ሪፖርቱ በተቃውሞ ላይ የተገደሉ የቆሰሉናና የታሰሩ ህጻናት መኖራቸውንም የመንግሥታቱ ድርጅት ሪፖርት አመልክቷል፡፡

ኮሚሽነሯ በሱዳን ያለው የፖለቲካ ቀውስ በሰብአዊ መብቶች ላይ እጅግ አሳሳቢ ሥጋት ማስከተሉን በመግለጽ የሱዳን ባለሥልጣናት አገሪቱን በአስቸኳይ የህግ የበላይነት ወደ ሰፈነበትና የሲቪል አስተዳደር ወደነበረበት እንዲመልሱ የሱዳን ህዝብ ፍትህ እኩልነትና ሰላም እንዲያገኝ አሳስበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG