ባለፈው ሳምንት ዐርብ ባርሴሎና ከተማ ውስጥ ያረፉት የቀድሞው የአንጎላ ፕሬዚዳንት ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ አስከሬን እንዲመረመር በስፔይን ፍ/ቤት ተፈቅዷል።
አሟሟታቸውን በሚመለከት የምጠራጠረው ነገር ስላለ አስከሬናቸው ይመርመርልኝ በማለት የዶስ ሳንቶስ ሴት ልጃቸው ቺዜ ጠይቀዋል።
ቲቼ "በመጪው ምርጫ ተቃዋሚዎችን እንዳይደግፍ የሚፈልጉ የፖለቲካ ጠላቶች ነበሩት" ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
የቀድሞው ፕሬዚዳንት የፈለጉት ቀብራቸው ስፔይን ውስጥ እንዲከናወን ቢሆንም አንጎላ አስከሬናቸው ወደሀገራቸው ተወስዶ መንግሥታዊ የቀብር ስነ ስርዓት ለማካሄድ ተንቀሳቅሳለች።
የሰባ ዘጠኝ ዓመቱ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ ለረጅም ጊዜ ታምመው እንደነበር እና ሲታከሙ በቆዩበት ባርሴሎና በሚገኝ ሆስፒታል ህይወታቸው ማለፉን ከፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ አመልክቷል።