በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊያ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት ቢያንስ 9 ሰዎች ተገደሉ


ሞቃዲሾ ውስጥ በደረሰ የአጥፍቶ ማጥፋት የፍንዳታ ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች ሞቱ
ሞቃዲሾ ውስጥ በደረሰ የአጥፍቶ ማጥፋት የፍንዳታ ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች ሞቱ

ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ውስጥ ዛሬ ረቡዕ በተሽከርካሪ መኪና ላይ በተጠመደው የአጥፍቶ ማጥፋት የፍንዳታ ጥቃት ቢያንስ 9 ሰዎች መገደላቸውና ሌሎች 9 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ተገለጸ፡፡

ጥቃቱ የደረሰው በሞቃድሾ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በቡድን ይጓዝ በነበረ የመንግሥት ደህንነት ተሽከርካሪዎች ቡድን ላይ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የዓይን እማኞች በከፍተኛው ፍንዳታ በአቅራቢያው በነበሩ ህንጻዎችና ቆመው የነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል፡፡

የሶማሊያ ፖሊስ ቃል አቀባይ ሀሰን አሊ በአደጋው 9 ሰዎች መገደላቸውንና ሌሎች 9 ደግሞ መቁሰላቸውን አስታውቀዋል፡፡

በተሽካሪዎች ውስጥ ከነበሩትና ከሞቱት መካከል አንዱ የሞቃዲሾ ረዳት ከንቲባ አሊ ያሬ አሊ እንደሚገኙበት ሲገልጽ ይህ የሟቾቹን ቁጥሩን 10 እንደሚያደርሰው ተዘግቧል፡፡

የቪኦኤ ዘጋቢ ለመንግሥት ቅርበት ያላቸው ምንጮችን ጠቅሶ ከቦታው እንደዘገበው በተሽክርካሪዎቹ ውስጥ እነማን እንደነበሩ ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ አልታወቀም፡፡

ሌሎች የዐይን እማኞች የጥቃቱ ኢላማ የነበረው በአቅራቢያው ሲያልፍ የነበረ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተሽከርካሪዎች ቡድን መሆኑን መግለጻቸውም ተመልክቷል፡፡

ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደው አልሸባብ ጥቃቱ ኢላማ የተደረጉት የሶማልያ መንግሥትና የውጭ አገርና ባለሥልጣናትን መሆናቸውን አመልክቷል፡፡

በሞቃዲሾ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ድርጊቱን አውግዟል፡፡ በሶማሊያ ለረጅም ጊዜ ሲተላለፍ የቆየው የምክር ቤት አባላት ምርጫ እኤአ የካቲት 25 እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG