በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትሩን አገዱ


የሶማሌ ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሁሴን
የሶማሌ ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሁሴን

የሶማሌ ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሁሴን ሮቤልን ከሥልጣን ማገዳቸውን አስታወቁ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ጥሩ የሥራ ግንኙት የሌላቸው ሲሆን፣ የተቻኮለ እርምጃዎችንም ይወስዳሉ ሲሉ ከሰዋቸዋል፡፡

በቅርቡ አድራሻቸው በጠፋው የደህንነት ሠራተኛዋ ኢክራን ታህሊል ፋራህ ጉዳይ በፕሬዚዳንቱና በጠቅላይ ሚኒስትሩ መካከል ከፍተኛ አለመግባባት መፈጠሩ ይታወሳል፡፡

እኤአ ከጥር 26 ጀምሮ የተሰወሩትን ሠራተኛ የቀጠራቸው የአገሪቱ ብሄራዊ የደህንነት ተቋም ኢክራን በአልሸባብ የተገደሉ ናቸው ቢሉም አልሸባብ ግን ክሱ አስተባብሏል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት የፕሬዚዳንቱን ውሳኔ አስመልክቶ እስካሁን በጉዳዩ ላይ ምላሽ አልሰጠም፡፡ ይሁን እንጂ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለቪኤ እንደተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ሮቤል በቅርቡ ለሶማሊያ ህዝብ ያላቸውን አስተያየት ይገልጻሉ፡፡

XS
SM
MD
LG