በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማልያ መሪዎች በምርጫው ሰሌዳ አልተስማሙም


ፎቶ ፋይል፦ የሶማልያ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ
ፎቶ ፋይል፦ የሶማልያ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ

የሶማልያ ተቋማዊ ቡድኖች፣ የፕሬዚዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ መንግስት፣ ምርጫው እንዲዘገይ ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃወም፣ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ፣ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡

ለፕሬዚዳንታዊ የሶማልያ ምርጫ የሚወዳደሩት የተቃዋሚ ፓርቲዎች እጩዎች ህብረት፣ የሶማልያን መንግሥት ፕሬዚዳንት አመራር እንደሚቃወሙ አስታውቀዋል፡፡

ፈርማጆ በሚል የቅጽል መጠሪያቸው የሚታወቁት የሶማልያው ፕሬዚዳንት ሌላ የአራት ዓመት ተጨማሪ የሥልጣን ዘመን የሚፈልጉ ቢሆንም የሶማልያ ምክር ቤት ግን ማራዘሚያውን ውድቅ አድርጎታል፡፡

የፕሬዚዳንት ፋርማጆ የሥልጣን ዘመን ያበቃው ባለፈው ሳምንት ቢሆንም፣ ምንም ዓይነት የምክር ቤት ምርጫ ስለመኖሩ ይፋ አልተደረገም፡፡ የሳቸውም መንግሥትና ባለሥልጣናት ስለሁኔታው ያስታወቁትም ሆነ የሰጡት ፍንጭ የለም፡፡

የሶማልያው መሪዎች በምርጫው ሰሌዳ አልስተማሙም
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:40 0:00

የተቃዋሚዎቹ ፕሬዚዳንታዊ ዕጩዎች ህብረት ሊቀመንበር፣ ሼኽ ሸሪፍ አህመድ በምክር ቤቱ ህንጻ ፊት ለፊት ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት የተቃውሞ ሰልፉ የሚደረገው መንግሥት በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ምርጫውን ባለማካሄዱ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡ ሼኽ አህመድ አስከትለውም

“የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በዚህ ሳምንት አርብ የፈደራል መንግሥቱን በመቃወም ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ ተስማምተዋል፡፡ ምክንያቱም የፌደራል መንግሥቱ ግልጽ የሆነ ምርጫ ማድረግ አልቻለም፣ የአገሪቱን ደህንነትም ማስጠበቅና በአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ መረጋጋትን አላመጣም፡፡”

ፕሬዚዳንታዊ ሥልጣኑን ከሚሹት መከካል አንዱ የሆኑት፣ የቀደሞ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ መሀመድ፣ ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ ዓለም አቀፎቹ አጋሮች፣ ሶማልያ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊት አገር እንድትሆን እንዲያግዟት ተማጽነዋል፡፡ ሞሀመድ ከዓለም አቀፉ ማህበረስብ ምን እንደሚጠብቁም ሲናገሩ

“ከዓለም አቀፍ ተቋማት የምንጠብቀው የመፍትሄው አካል እንጂ የችግሩ አካል እንዳይሆኑና፣ የሶማልያን ጉዳይ እያወሳሰቡ ያሉትን የፖለቲካ መሪዎች ሁሉ በማነጋገር የመፍትሄው አካል እንዲያደርጓቸው ነው፡፡”

ችግሩ እየተባባሰ ባለበት ሁኔታ ውስጥ፣ የፖለቲካ መሪዎች ፣ ውጥረት የበዛበትንና በቋፍ ያለውን የአገሪቱ ሁኔታ የበለጠ ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ቡድኖች አሳስበዋል፡፡

ከእነዚህ መካከል የአፍሪካ ቀንድ የሰላምና ልማት ተቋም ድሬክተር ሀሰን ሙዳኔ አንዱ ናቸው፡፡

“ፕሬዚዳንት ፎርማጆ ምርጫውን በጊዜው ሰሌዳ መሠረት ማድረግ አለመቻላቸው ግልጽ ነው፡፡ በሌላም በኩል ተቃዋሚዎችም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአገሪቱ እየተስፋፋ ባለበት በዚህ ወቅት የተቃውሞ ሰልፍ መጥራታቸው ልክ ኃላፊነት የጎደለው ነገር ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ በሶማልያ ዋና ከተማ ሞቃድሾ የቦንብ ጥቃት ሊደርስ እንደሚችል ስጋት መኖሩ ተገልጿል፡፡”

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ፣ ሁሉም የሶማልያ መሪዎች የተናጥል እምርጃዎችን እንዳይወስዱ አሳስቧል፡፡ ይልቁንም፣ እኤአ መስከረም 2020 ምርጫውን አስመልክቶ 101 የምክር ቤት አባላትን ለማስመረጥና ከዚያም ውስጥ የአገሪቱን ርዕሰ ብሄር ለመምረጥ የደረሱበትን ስምምነት በቶሎ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡

የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ፈርማጆ በበኩላቸው ከስምምነቱ ያፈነገጡት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው በማለት ይከሳሉ፡፡ (የቪኦኤ ዘጋቢ ሞሀመድ ካዬ ከሞቃድሾ ከላከው ዘገባ የተወሰደ፡፡)

XS
SM
MD
LG