በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞቃዲሾ ውስጥ ፖሊሶች በአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ጥቃት ተገደሉ


ትናንት ዕሁድ ማታ ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ውስጥ አጥፍቶ ጠፊ ባፈነዳው ቦምብ ቢያንስ ስድስት ሰዎች ተገደሉ፤ አምስቱ ፖሊሶች መሆናቸው ታውቋል።

የሶማሊያ ፖሊስ ቃል አቀባይ ሻለቃ አህመድ አብደላሂ ባሳኔ ከተገድሉት መካከል ሁለቱ የፖሊስ አዛዦች መሆናቸውን አረጋግጠዋል። አንደኛው የተገደለው ሲቪል ፖሊስ ጣቢያው አጠገብ የሚኖር እንደነበር ተገልጿል።

እማኞች እንዳሉት አጥፍቶ ጠፊው ዋቤሪ ፖሊስ ጣቢያ ፖሊሶቹ አጠገብ ተጠግቶ በሰደሪያ የታተቀውን ቦምብ አፈንድቶታል፤ ለቦምብ ጥቃቱ የሶማሊያ ባለሥልጣናት አልሻባብን ወንጅለዋል።

XS
SM
MD
LG