በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ የአል-ሻባብ አዛዥ ሚኒስትር ሆኑ

የቀድሞው የአልሸባብ ምክትል አዛዥ የነበሩት ሙክታር ሮቦው፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ አብዲ ባሬ የሃይማኖት ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በኋላ በባልደረባዎች መካከል ተቀምጠው፤ ሶማሊያ፣ ሞቃዲሾ እአአ ነሃሴ 2/2022
የቀድሞው የአልሸባብ ምክትል አዛዥ የነበሩት ሙክታር ሮቦው፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ አብዲ ባሬ የሃይማኖት ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በኋላ በባልደረባዎች መካከል ተቀምጠው፤ ሶማሊያ፣ ሞቃዲሾ እአአ ነሃሴ 2/2022

የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ አብዲ ባሬ የአልሸባብ ምክትል አዛዥ የነበሩትን ሙክታር ሮቦውን ለካቢኔያቸው አባልነት መርጠዋል።

ከፕሬዚዳንቱ፣ ከእንደራሴዎችና ከሌሎችም ወገኖች ጋር ለ35 ቀናት ካደረጉት ውይይት በኋላ ትናንት ሞቃዲሹ ላይ ካቢኒያቸውን ሲያሳውቁ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ ሮቦውን የሃይማኖት ጉዳዮች ሚኒስትር አድርገው መሾማቸውን የተናገሩት።

አል-ሸባብን ከድተው እጃቸውን በ2009 ዓ.ም. የሰጡት ሮቦው ወይም በሌላ ስማቸው አሊ አቡ ማንሱር ላለፉት ሦስት ዓመታት በቁም እሥር ላይ ነበሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሶማሊያ መልከ ብዙ ችግሮች ላይ በመሆኗ ለሥራው የሚመጥን መንግሥት ያስፈልጋታል” ብለዋል።

ሙክታር ሮቦው ለደቡብ ምዕራብ ግዛት ፕሬዚዳንትነት ምርጫ ውድድር ገብተው የነበረ ጊዜ ግን ወደ ወኅኒ ተልከው ነበር።

XS
SM
MD
LG