በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያ ፍ/ቤት የአልሻባብ አባላት ላይ የእስር ቅጣት ሰጠ


ፎቶ ፋይል፦ ሞቃዲሾ ከተማ
ፎቶ ፋይል፦ ሞቃዲሾ ከተማ

የሶማሊያ ፍርድ ቤት የውጭ ሃገር ዜጎች በሆኑ የአልሻባብ አባላት ላይ የእስር ቅጣት ሰጠ።

አንድ የእንግሊዝ እና አንድ ማሌዥያ ዜጋ የአስራ አምስት ዓመት እስራት ቅጣት ተወስኖባቸዋል።

ሞቃዲሾ ላይ ያስቻለው የጦር ፍርድ ቤቱ ዴረን አንተኒ ባይርንስ የተባለውን እንግሊዛዊ እና አህመድ ሙስታኪም አብደልሃሚድ የተባለው ማሌዥያዊ የጽንፈኛው ታጣቂ ቡድን የአልሻባብ አባል በመሆን እና በህገ ወጥ መንገድ ሶማሊያ በመግባት እያንዳንዳቸው በአስራ አምስት ዐመት እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።

በሀገሪቱ የውጭ ሃገር ዜጎች ላይ በፍርድ ቤት ቅጣት ሲወሰን ይህ የመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የፍርድ ቤት ባለሥልጣናት ገልጸዋል።

አቃቤ ህግ ሰዎቹ አልሻባብን በመደገፍ ሃገራችንን ሊያወድሙ እና የህዝብ ደም ሊያፈሡ ገብተዋል ብሏል፥ ጠበቃቸው በበኩላቸው የቡድኑ አባላት አይደሉም፥ ዘመድ ሊጠይቁ የሄዱ ናቸው ብለው ተከራክረዋል፥ ይግባኝ እንደሚጠይቁም ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG