በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማልያ በደረሱ ጥቃቶች የአሁኑና የቀድሞ ምክር ቤት አባላት ተገደሉ


ባልደዌን ከተማ ሶማልያ
ባልደዌን ከተማ ሶማልያ

በማዕከላዊ ሶማልያ በባልደዌን ከተማ ትናንት በደረሱት ጥቃቆች የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 15 ማደጉን የአገሪቱ መንግሥት ቴሌቪዥን አስታውቋል፡፡ ከተገደሉት ውስጥ ለፓርላማ ምርጫ እጩ ተወዳዳሪ በአካባቢው የምረጡኝ ዘመቻ ሲያካሂዱ የቆዩት አሚና ሞሀመድ አብዲ እንደሚገኙበት ተነገሯል፡፡

አሚና የሞቱት የአጥፍቶ መጥፋቱን ፍንዳታ ያደረሰው ሰው እርሳቸው ወደሚገኙበት ተሽከርካሪ ዘሎ በመግባት ራሱንና ተሽከርካሪውን አብሮ በማፈንዳቱ መሆኑ ተገልጿል፡፡ አሚና አብዲ የሶማልያ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ ተቃዋሚ የነበሩ ሲሆን ቀደም ሲል በተገደሉት የደኅንነት ሚኒስትር ባልደረባ ሴት ሞት ፕሬዚዳንቱን አብዝተው ይኮንኗቸው እንደነበር ተነግሯል፡፡

በሌላም በኩል እዚያ ከተማ ውስጥ በደረሰ ሌላ ጥቃት የቀድሞ የፓርላማ አባል የሆኑት አሊ አብዲ ድኹል የተገደሉ ሲሆን የቀድሞ የትምህርት ሚኒስትር የነበሩት ዳኺር ኦስማን መቁሰላቸው ተመልክቷል፡፡

ለሁለቱ ጥቃቶቹ እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ የለም፡፡

ይሁን እንጂ ፍንዳታዎቹ የደረሱት በሶማልያ መዲና ሞቃድሾ በሚገኘው ኤደን አዴ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የአልሸባብ ታጣቂዎች ጥቃት ባደረሱ ጥቂት ሰዓታት ውስጥ መሆኑን ፖሊስ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የአውሮፕላን ማረፊያው ጥቃቅ የተፈጸመው በሶማልያ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ አሚሶም ወታደሮች ይጠበቅ በነበረው ተቋም ሲሆን፣ በጥቃቱ ከተገደሉት ውስጥ ሁለት የውጭ አገር ወታደራዊ አሰልጣኞችና አንድ የሶማልያ ዜጋ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

አልሻባብ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG