በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያ የዕሁዱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሚካሄድበት አጠገብ አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ፍንዳታ ደረሰ


በሶማሊያ ሞቃዲሾ በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ፍንዳታ ቢያንስ ሰባት ሰዎች መቁሰላቸውን የሶማሊያ ፖሊስ አስታወቀ።
በሶማሊያ ሞቃዲሾ በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ፍንዳታ ቢያንስ ሰባት ሰዎች መቁሰላቸውን የሶማሊያ ፖሊስ አስታወቀ።

የፊታችን ዕሁድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ሊካሄድ በታቀደበት የሞቃዲሾ አውሮፕላን አቅራቢያ ዛሬ ረቡዕ በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ፍንዳታ ቢያንስ ሰባት ሰዎች መቁሰላቸውን የሶማሊያ ፖሊስ አስታወቀ። ሌሎች የፖሊስ ምንጮች በበኩላቸው በፍንዳታው ሁለት የጸጥታ ጥበቃ አባላት ያሉባቸው ቢያንስ ሦስት ሰዎች ተገድለዋል ብለዋል።

የፖሊስ ቃል አቀባዩ አብደልፋታህ አዳን ሃሰን በሰጡት ቃል የጥቃቱ ኢላማ በወቅቱ በአንድ ብረት ለበስ ወታደራዊ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩት ከፍተኛ ጀነራል እንደነበሩ ገልጸዋል። ጄኔራል ጋራቤይ በጥቃቱ ሳይጎዱ መትረፋቸውን ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

ከአልቃይዳ ጋር ቁርኝት ያለው አልሸባብ ለጥቃቱ ኃላፊ ነኝ ብሏል።

ጥቃቱ የደረሰው ለረጅም ጊዜ ሲጓተት የቆየው የሶማሊያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የፊታችን ዕሁድ ሊካሄድ አራት ቀን ሲቀረው መሆኑ ነው።

የሀገሪቱ ምክር ቤት በአውሮፕላን ጣቢያው ግቢ በከፍተኛ ጥበቃ ተሰባስበው ቀጣዩን ፕሬዚዳንት ይመርጣሉ። በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ለመወዳደር አሁን ሥልጣን ላይ ያሉትን ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ፋርማጆን ጨምሮ ካሁን ቀደም ባልታየ መጠን ቁጥራቸው ብዙ የሆነ ሠላሳ ዘጠኝ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ተመዝግበዋል።

XS
SM
MD
LG