በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ህብረትና ዩናይትድ ስቴትስ የአልሸባብን ጥቃት አወገዙ


ፎቶ ፋይል፦ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች በሞቃዲሾ፣ እአአ ሚያዚያ 27/2022
ፎቶ ፋይል፦ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች በሞቃዲሾ፣ እአአ ሚያዚያ 27/2022

የአፍሪካ ህብረትና ዩናይትድ ስቴትስ አልሸባብ ተዋጊዎች ሶማሊያ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ጦር ሠፈር ላይ ጥቃት በማድረስ 173 ወታደሮች ገድለናል ብለው በትናንትናው እለት ያስታወቁትን ጥቃት አወገዙ፡፡

በሞቃድሾ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ ለሶማልያ መረጋጋት ሲባል ከአፍሪካ ህብረትና የሶማልያ ኃይሎች ጋር በአጋርነት እንደሚሰራ ገልጾ ጥቃቱን እንደሚያወግዝ አስታውቋል፡፡

ቀደም ሲል የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ማሃማት በጥቃቱ ለሞቱ የወታደሮቹ ቤተሰቦች ጥቅል ሀዘናቸውን ገልጸዋል፡፡ ህብረት በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ያለውን ቁርጠኝነትም እንደሚቀጥልበት በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡

አልሻባብ በጥቃቱ ከ170 በላይ ወታደሮች መግደሉን ትናንት ማክሰኞ አስታውቋል፡፡ በጥቃቱ ቢያንስ 30 የብሩንዲ ወታደሮችን ሲሞቱ ሌሎች መቁሰላቸው ተነግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG