በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሱ ፕሬዚዳንት የተከፋፈለች እና ግማሽ ሚሊዮን ሕዝቧ በድርቅ የተጎዳባት ሶማሊያን ተረክበዋል


አዲሱ ፕሬዚዳንት የተከፋፈለች እና ግማሽ ሚሊዮን ሕዝቧ በድርቅ የተጎዳባት ሶማሊያን ተረክበዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:54 0:00

አዲሱ ፕሬዚዳንት የተከፋፈለች እና ግማሽ ሚሊዮን ሕዝቧ በድርቅ የተጎዳባት ሶማሊያን ተረክበዋል

ከሳምንት በፊት በሶማሊያ በተደረገ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ የነበሩት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ትናንት በትረ ሥልጣናቸውን ሲረከቡ በሃገሪቱ ታሪክ በድጋሚ ተመልሰው የፕሬዚዳንትነቱን ወንበር የተረከቡ የመጀመሪያው መሪ ሆነዋል።

እአአ ከ2012 እስከ 2017 ሃገሪቱን በፕሬዚዳንትነት መርተው የነበሩት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ትናንት በሃገሪቱ መዲና ሞቃዲሹ ውስጥ በተደረገ አጭር ሥነ ስርዓት መንበሩን በምርጫ ካጡትና “ፎርማጆ” በመባል ከሚታወቁት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ ተረክበዋል።

በሦስት ዙር በተደረገና ከፍተኛ ፉክክክር በታየበት ያለፈው ሳምንት ምርጫ የቀድሞውን የሃገሪቱ ፕሬዘዳንት ፎርማጆ ያሸነፉት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ በሃገሪቱ ታሪክ ተመልሰው ስልጣን የጨበጡ መሪ ሆነዋል።

ሞሃመድ ዳይሴን ለቪኦኤ እንደዘገበው አጭር ግን ደማቅ በነበረውና በመዲናዋ ሞቃዲሾ በተደረገ ሥነ ስርዓት አዲሱ ፕሬዚዳንት መንበረ ሥልጣናቸውን ከተሸናፊው ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ በቅፅል ስማቸው “ፎርማጆ” ተረክበዋል።

ፎርማጆ በሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የሶማሊያ ህዝብ አዲሱን ፕሬዚዳንት እንዲደግፍ ጥሪ አድርገዋል።

“የሶማሊያ ህዝብ ከአዲሱ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ጋር እንዲሰራ እመክራለሁ፤ ምክንያቱም ምርጫው ተጠናቋል። ሥራቸውንም ይጀምራሉ፤ የሚሰሩት ሁሉ ለሶማሊያ ህዝብ ይሆናል” ብለዋል።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ፎርማጆ የሶማሊያ ወታደሮች በኤርትራ እንደሚገኙ ለመጀመሪያ ግዜ ይፋ አድርገዋል። ወታደሮቹ የተላኩት ለሥልጠና ቢሆንም በሰሜን ኢትዮጵያ ሲካሄድ በነበረው ጦርነት ተሳትፈዋል የሚል ክስ ሲቀርብባቸው ነበር።

አዲሱ ፕሬዘዳንትም በሥነ ስርዓቱ ላይ በኤርትራ ስለሚገኙት የሶማሊያ ወታደሮች ጉዳይ ሲናገሩ “ዛሬ ታሪካዊ ቀን ነው። ሥልጣኑንም ሆነ የመንግሥት ዶሴዎችን በሰላም ተረክቤያለሁ። በኤርትራ የሚገኙ ሰልጣኝ ወታደሮቻችንም ወደ ሶማሊያ እንዲመለሱ እንሰራለን” ብለዋል።

በኤርትራ የሚገኙት የሶማሊያ ወታደሮችን ቁጥር በተመለከተ እስከ አሁን በሚስጥር ተይዞ ቆይቶ ነበር። ባለሥልጣናት ወደ 5 ሺሕ ወታደሮች እንደተላኩ ይናገራሉ። አንዳንድ የወታደሮቹ ወላጆችም ልጆቻቸው ያሉበትን ለማወቅ በሰላማዊ ሰልፍ ሲጠይቁ እናደነበር ይታወሳል።

ለረጅም ግዜ ሲተላልፍ በቆየው ምርጫ ሳቢያ ሶማሊያ በፖለቲካ ፍጥጫ ውስጥ ቆይታ የነበረ ቢሆንም የተደረገው ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር የነበረውን የፖለቲካ አለመረጋጋት እልባት ይሰጠዋል የሚል ዕምነት አሳድሯል።

እአአ ከ2012 እስከ 2017 ሃገሪቱን በፕሬዚዳንትነት መርተው የነበሩትና ባለፈው ሳምንት ምርጫ በድጋሚ የተመረጡት አዲሱ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ የተረከቧት ይበልጥ የተከፋፈለች፣ እንዲሁም በድርቅ ሳቢያ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ህዝቦች የተፈናቀለባትን ሶማሊያ ነው።

XS
SM
MD
LG