በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊያ 300ሺ ሰው በቸነፈር ሊመታ ይችላል - ፋኦ


ፎቶ ፋይል፦ በድርቅ የተጠቃው የታችኛው ሸበሌ አካባቢ ሸሽተው፣ በሶማሊያ ሞቃዲሾ ወጣ ብሎ በሚገኝ የተፈናቃዮች መጠለያ የሚገኙ ቤተሰቦች፣ በምግብ እጥረት የተጎዳ ልጇን ታቅፋ
ፎቶ ፋይል፦ በድርቅ የተጠቃው የታችኛው ሸበሌ አካባቢ ሸሽተው፣ በሶማሊያ ሞቃዲሾ ወጣ ብሎ በሚገኝ የተፈናቃዮች መጠለያ የሚገኙ ቤተሰቦች፣ በምግብ እጥረት የተጎዳ ልጇን ታቅፋ

የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) በሶማሊያ ከ300 ሺ በላይ የሚሆን ሰው በቸነፈር ይመታል ሲል አስጠንቅቋል።

ጄኔቭ ከሚገኘው ቢሮው ሪፖርቱን ያወጣው ፋኦ እንዳለው፣ በዚህ ዓመት በሶማሊያ 6.7 ሚሊዮን ሠው ጠንከር ያለ ረሃብ ሊገጥመው ይችላል።

ሊሳ ሽላይን ከጄኔቭ በላከችው ዘገባ መሰረት፣ በቸነፈር ሊመቱ ይችላሉ ተብለው የተሰጉት በባይዶዋና በበርሃካባ ግዛት የሚገኙ፣ እንዲሁም በደቡብ ሶማሊያ ባህረ ሰላጤ የምትገኘው ባይዶዋ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች ናቸው።

“በተደጋጋሚ የተሰጡት ማስጠንቀቂያዎች ግልጽ ናቸው፤ አሁኑኑ እርምጃ ይወሰድ፣ አለዛ በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ቸነፈር ይከሰታል” ሲሉ በሶማሊያ የፋኦ ተወካይ ኤትየን ፒተርሽሚት ተናግረዋል።

ድርቁ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው ሲሉም አክለዋል።

ፒተርሽሚት ይህን ያሉት በሰሜን ምሥራቅ ሶማሊያ ፑንትላንድ ግዛት ውስጥ በካባላ አውራጃ ድርቁ በእንስሳት አርቢዎች ላይ ያስከተለውን ጉዳት በመገምገም ላይ እያሉ ነው። ለረጅም ግዜ ታይቶ የማይታወቅ የከፋ ድርቅ፣ የምግብ ዋጋ መናር፣ እና ግጭት የምግብ ዋስትናን እጅግ አሳሳቢ ደረጃ አውርዶታል ብለዋል።

ድርቁ በተለይ በህፃናት ላይ ከፍተኛ አደጋ አድርሷል።

የህፃናት አድን ድርጅቱ ዩኒሴፍ እንደሚለው ከአስር ዓመት በፊት በነበረው ቸነፈር 340 ሺህ ህፃናት ለተመጣጠነ ምግብ እጦት ችግር ሲጋለጡ፣ አሁን ባለው የድርቅ ወቅት በችግሩ የሚሰቃዩት ህፃናት ቁጥር ወደ 513 ሺህ አሻቅቧል።

XS
SM
MD
LG