በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሌ ክልል ተፈናቃዮችን ለማቋቋም ዕቅድ ወጣ


የሶማሌ ክልል ተፈናቃዮችን ለማቋቋም ዕቅድ ወጣ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:50 0:00

የሶማሌ ክልል ተፈናቃዮችን ለማቋቋም ዕቅድ ወጣ

በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ካትሪን ሶዚ የተመራ የ5 ሃገሮች አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች የሚገኙበት ቡድን የሶማሌ ክልል ተፈናቃዮች በሚቋቋሙበት ሁኔታ ላይ ከክልሉ ባለሥልጣናት ጋር መክሯል።

ለመልሶ ማቋቋሚያ ዕቅዱ ክልሉ የ129 ሚሊዮን ደላር ዕቅድ አቅርቧል።

በዶ/ር ሶዚ የተመራው ቡድን የኢጣልያ፣ የጃፓን፣ የስዊትዘርላንድ፣ የቼክ ሪፐብሊክና የፊንላንድ አምባሳደሮች እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ /ዩኤስኤአይዲ/፣ የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት አጣዳፊ ድጋፍ ፈንድ /ዩኒሴፍ/፣ የምግብና ግብርና ድርጅት /ፋኦ/ና የዓለምአቀፍ ፍልሰት ጉዳዮች ድርጅት /አይኦኤም/ ተወካዮች የሚገኙበት ነው።

ከርዕሰ መስተዳድሩ ሙስጠፋ መሀመድ ጋር ጂጂጋ ውስጥ የተወያዩት ዓለም አቀፍ ልዑካን በማቋቋሙ ሥራ ክልሉን ለማገዝ ያላቸውን ዝግጁነት መግለፃቸውን የኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮው ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል።

በግጭትና በድርቅ ምክንያት የተፈናቀሉ መቶ ሺህ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የተገለፀው ዕቅድ የአየር ንብረት ለውጥን ተፅዕኖ ለመቋቋምና አስቸኳይ ድጋፍ ለመስጠት የታሰበ ሲሆን በሦስት ዓመት ውስጥ በሚከናወኑ ተግባራት ተፈፃሚ እንደሚደረግ የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ፈርሃን ጂብሪል አመልክተዋል።

በቅርብ ሣምንታት ዩኤስኤአይዲን ጨምሮ የተለያዩ የረድዔት ድርጅቶች ተጠሪዎችና አምባሳደሮች በሶማሌ ክልል በድርቅ ምክንያት የተፈናቀሉና ከ4 ዓመት በፊት ከኦሮምያ ክልል ተፈናቅለው በቆለጂ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙትን ጎብኝተው እንደነበረ ተዘግቧል።

ዘገባው የአዲስ ቸኮል ነው።

XS
SM
MD
LG